አይደለህም ፡ እንደሰው (Aydelehem Endesew) - ዳግማዊ ፡ ጥላሁን ፡ እና ፡ ሳሙኤል ፡ ተስፋሚካኤል

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
ዳግማዊ ፡ ጥላሁን ፡ እና ፡ ሳሙኤል ፡ ተስፋሚካኤል
(Dagmawi Tilahun)

Lyrics.jpg

ልዩ ፡ እትም
(Esp)

Liela Liela Liela
(Liela Liela Liela)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ (2007)
ቁጥር (Track):

(4)

ርዝመት (Len.): 6:05
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የዳግማዊ ፡ ጥላሁን ፡ እና ፡ ሳሙኤል ፡ ተስፋሚካኤል ፡ አልበሞች
(Albums by Dagmawi Tilahun)

አይደለህም እንደሰው አይደለህም ጌታዬ
አይደለህም እንደሰው አይደለህም አምላኬ

አንተ ሊወድቅ የዘመመን በእጅህ አቅንተህ አለህ
አንተ የማዐዘን ድንጋይ እራስ ሆነህ አለህ
አንተ ጉልበተኛ ሞቶ ሊገፋው ቡሞክር
ባንተ ሃይሉ ከንቱ ሆኖ አየሁት ሲያፍር

ለደሃደግ ወዳጅ ለተገፋው አዛኝ
እኔስ እንደ አንተ ፈፅሞ አላየሁም/4

አይደለህም እንደሰው አይደለህም ጌታዬ
አይደለህም እንደሰው አይደለህም አምላኬ

አንተ የተቀጠቀጠውን ሸንበቆ አትሰብርም
አንተ የተጎዳውን ልብ ዝም ብለህ አታልፍም
አንተ በሃሜት በወሬ ውስጡ ለደቀቀ
አንተ ትጠግነዋለህ አድርገህ ሌላ ሰው

ከጥንት የምትሰራ ድንቅ ነው ልማድህ
ደመና ቀደህ ትወርዳለህ ፈጣን ነህ እኔን ለመርዳት/2

አይደለህም እንደሰው አይደለህም ጌታዬ
አይደለህም እንደሰው አይደለህም አምላኬ

አንተ ከሰፈር መንደሩ ወቶ ለተገለለ
አንተ በቃ የሱ ነገር ሞቷል የተባለ
አንተ ያለፈውን ችግር ሁሉ አስረስተኸው
አንተ በመካራው ሃገር ይኸው አፈራኸው

ደለደልከው ያንን ተራራ አወጣኸኝ ከዛ መከራ
ለውጥከው አንተ ኑሮዬን ዛሬን አይሁኝ ጌታዬ
ደለደልከው ያንን ተራራ አወጣኸኝ ከዛ መከራ
ተለወጠ ባንተ ኑሮዬ ተመስገንልኝ ጌታዬ

ደግሞ ልቤ አርፎ ተደላድሎ ይኖራል
አንተን ተስፋ ያደርጋል

ከፊትለፊቴ ቆሞ ያስለቀሰኝ ተራራ
ሁሌ ይምስለኝ ነበር የሚፈርስ በተራ
አንተ ግን ከሰማይ ቃልህን ስትልከው
ትልቁን ተራራ በአንዴ ነቀልከው ከስሩ ነቀልከው

አይደለህም እንደሰው አይደለህም ጌታዬ
አይደለህም እንደሰው አይደለህም አምላኬ