አያለሁ (Ayalehu) - ዳግማዊ ፡ ጥላሁን ፡ እና ፡ ሳሙኤል ፡ ተስፋሚካኤል

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ዳግማዊ ፡ ጥላሁን ፡ እና ፡ ሳሙኤል ፡ ተስፋሚካኤል
(Dagmawi Tilahun)

Lyrics.jpg

ልዩ ፡ እትም
(Esp)

ሌላ ፡ ሌላ ፡ ሌላ
(Liela Liela Liela)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ (2007)
ቁጥር (Track):

(2)

ርዝመት (Len.): 6:10
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የዳግማዊ ፡ ጥላሁን ፡ እና ፡ ሳሙኤል ፡ ተስፋሚካኤል ፡ አልበሞች
(Albums by Dagmawi Tilahun)

የኑሮ ፡ መክበዱን ፡ ሁሉ ፡ ነገር ፡ መወደዱ
እህል ፡ ከጐተራ ፡ ሲጠፋ ፡ ፍሬም ፡ ባትሰጥ ፡ መሬት ፡ ታርሳ
ቀና ፡ ብሎ ፡ ዓይን ፡ ሲያይ ፡ ደመና ፡ የለም ፡ በላይ
ምድር ፡ ከሰማይ ፡ ይጠብቃል ፡ ሰማይ ፡ በምድር ፡ ላይ ፡ አፍጡዋል
ጊዜው ፡ ቢወስድ ፡ ይህ ፡ ዝምታ ፡ አምላኬ ፡ ምድሬን ፡ እየረሳ
ግን ፡ ጨለማው ፡ መበርታቱ ፡ ሊነጋ ፡ ነው ፡ ሌሊቱ (፪x)

አዝ፦ አያለሁ ፡ አያለሁ ፡ ገና ፡ ኦ ፡ ገና ፡ ብዙ ፡ አያለሁ
አያለሁ ፡ አያለሁ ፡ ገና ፡ ኦ ፡ ገና ፡ ብዙ ፡ አያለሁ

የእግዚአብሔር ፡ ክንድ ፡ በምድሬ ፡ ሲነሳ
የመከራው ፡ ዘመን ፡ ሲረሳ
እምባ ፡ ካለቀሰው ፡ ሲታበስ
የዘመናት/የአባቶቼ ፡ ጸሎት ፡ ሲመለስ (፪x)
አያለሁ ፡ አያለሁ ፣ አያለሁ ፡ አያለሁ

አዝ፦ አያለሁ ፡ አያለሁ ፡ ገና ፡ ገና ፡ ገና ፡ ብዙ ፡ አያለሁ
አያለሁ ፡ አያለሁ ፡ ገና ፡ ኦ ፡ ገና ፡ ብዙ ፡ አያለሁ

የጦርነት ፡ ድምጽ ፡ ፈርቶ
ካደገበት ፡ ቀይ ፡ ሸሽቶ
በሰው ፡ ሃገር ፡ አንገት ፡ የደፋ
የተናቀን ፡ የተገፋ
ምድረ ፡ በዳውን ፡ ሲያቋርጠው
በረሃው ፡ ሁሉም ፡ ሱያስጥለው
ግን ፡ ሃገሩን ፡ ይዞ ፡ በልቡ
ተበትኗል ፡ ሰሜን ፡ ደቡቡ
ተስፋ ፡ ቢጨልም ፡ በሁሉ ፡ ነገር
አንደበት ፡ ግን ፡ ክፉ ፡ አይናገር
ያለፈው ፡ ይብቃ ፡ እርግማኑ
የምትሰማ ፡ አያለሁ (፪x)

አዝ፦ አያለሁ ፡ አያለሁ ፡ ገና ፡ ገና ፡ ገና ፡ ብዙ ፡ አያለሁ
አያለሁ ፡ አያለሁ ፡ ገና ፡ ኦ ፡ ገና ፡ ብዙ ፡ አያለሁ

ሽባዎች ፡ አንካሶች ፡ ሲዘሉ
ዲዳዎች ፡ ተናግረው ፡ ዕልል ፡ ሲሉ
የታወረው ፡ ዓይን ፡ ሲበራ
እግዚአብሔር/የማመልከው ፡ እራሱ ፡ ሲሰራ
አያለሁ ፡ አያለሁ ፣ አያለሁ ፡ አያለሁ (፭x)

ሃሌሉያ ፡ አያለሁ
እኔ ፡ እኔ ፡ እኔ ፡ አያለሁ