አሜን ፡ እላለሁ (Amen Elalehu) - ዳግማዊ ፡ ጥላሁን ፡ እና ፡ ሳሙኤል ፡ ተስፋሚካኤል

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ዳግማዊ ፡ ጥላሁን ፡ እና ፡ ሳሙኤል ፡ ተስፋሚካኤል
(Dagmawi Tilahun)

Lyrics.jpg

ልዩ ፡ እትም
(Esp)

ሌላ ፡ ሌላ ፡ ሌላ
(Liela Liela Liela)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ (2007)
ቁጥር (Track):

(7)

ርዝመት (Len.): 5:32
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የዳግማዊ ፡ ጥላሁን ፡ እና ፡ ሳሙኤል ፡ ተስፋሚካኤል ፡ አልበሞች
(Albums by Dagmawi Tilahun)

በጊዜው ፡ ነገር ፡ ሆድ ፡ አይብሰኝም
ምን ፡ አንዳሰበ ፡ ምንም ፡ አላውቅም
ልቤ ፡ ተስማማ ፡ አትክበድበት
ምክንያት ፡ ስላለው ፡ ይሁን ፡ ያለበት ፡ አሜን

አዝ፦ እስማማለሁ ፡ አሜን
ከአንተ ፡ ጋራ ፡ አሜን
ቢሆን ፡ ባይሆን ፡ አሜን
ልቤ ፡ አይፈራ
አሜን ፡ እላለሁ (አሜን) ፡ አሜን (፬x)

አልከራከርም ፡ ለምን ፡ ብዬ
ሲናገር ፡ አሜን ፡ ነው ፡ በተራዬ
ለእኔ ፡ የሚያስብልኝ ፡ ሁሉ ፡ በጐ
ከእኔ ፡ የሚፈልቀው ፡ አሜን ፡ ነው ፡ እኮ (፪x)

አዝ፦ እስማማለሁ ፡ አሜን
ከአንተ ፡ ጋራ ፡ አሜን
ቢሆን ፡ ባይሆን ፡ አሜን
ልቤ ፡ አይፈራ
አሜን ፡ እላለሁ (አሜን) ፡ አሜን (፬x)

ከዚህች ፡ አይምሮ ፡ ጥያቄ ፡ አምጥቼ
መከራከሬ ፡ ኧረ ፡ እስከመቼ
ያሰበው ፡ ካለ ፡ ከጥንት ፡ ያቀደው
እኔ ፡ ምን ፡ ገዶኝ ፡ አሜን ፡ እላለሁ

አዝ፦ እስማማለሁ ፡ አሜን
ከአንተ ፡ ጋራ ፡ አሜን
ቢሆን ፡ ባይሆን ፡ አሜን
ልቤ ፡ አይፈራ
አሜን ፡ እላለሁ (አሜን) ፡ አሜን (፬x)

አልከራከርም ፡ ለምን ፡ ብዬ
ሲናገር ፡ አሜን ፡ ነው ፡ በተራዬ
ለእኔ ፡ የሚያስብልኝ ፡ ሁሉ ፡ በጐ
ከእኔ ፡ የሚፈልቀው ፡ አሜን ፡ ነው ፡ እኮ (፪x)
አሜን ፡ እላለሁ (አሜን) ፡ አሜን (፬x)

ማስረጃ ፡ ልሻ ፡ ለሚለው ፡ ነገር
እሜን ፡ እላለሁ ፡ ምንም ፡ ቢናገር
ቀላባይ ፡ አይደል ፡ አቋም ፡ የሌለው
ከተናገረ ፡ ሊፈጽመው ፡ ነው ፡ አሜን

አዝ፦ እስማማለሁ ፡ አሜን
ከአንተ ፡ ጋራ ፡ አሜን
ቢሆን ፡ ባይሆን ፡ አሜን
ልቤ ፡ አይፈራ
አሜን ፡ እላለሁ (አሜን) ፡ አሜን (፬x)

አልከራከርም ፡ ለምን ፡ ብዬ
ሲናገር ፡ አሜን ፡ ነው ፡ በተራዬ
ለእኔ ፡ የሚያስብልኝ ፡ ሁሉ ፡ በጐ
ከእኔ ፡ የሚፈልቀው ፡ አሜን ፡ ነው ፡ እኮ (፪x)

አሜን
አሜን ፡ ነው ፡ እኮ...