ውለታው ፡ በዛ (Weletaw Beza) - ዳግማዊ ፡ ጥላሁን

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ዳግማዊ ፡ ጥላሁን
(Dagmawi Tilahun)

Lyrics.jpg


(1)

ጌታ ፡ እርሱ ፡ ብቻ ፡ ነው
(Gieta Esu Becha New)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ ፯ (2004)
ቁጥር (Track):

(7)

ርዝመት (Len.): 4:40
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የዳግማዊ ፡ ጥላሁን ፡ አልበሞች
(Albums by Dagmawi Tilahun)

እንደኔ ፡ ማነው ፡ የእኔስ ፡ ልዩ ፡ ነው
ወደቀ ፡ ሲባል ፡ ጌታ ፡ የሚያነሳው
ኢየሱስ ፡ ረድቶኛል ፡ በሁሉ ፡ አብልጦ
ከፍቶ ፡ አዲስ ፡ ምዕራፍ ፡ ታሪክ ፡ ለውጦ

አዝ፦ ውለታው ፡ በዛ ፡ ጌታ ፡ ውለታው ፡ በዛ
ውለታው ፡ በዛ ፡ ኢየሱስ ፡ ውለታው ፡ በዛ (፪x)

አቤት ፡ እንደኔ ፡ ማንን ፡ ረዳህ
አቤት ፡ እንደኔ ፡ ማንን ፡ አገዝክ
አቤት ፡ ምህረትህ ፡ የገነነለት
አቤት ፡ እንደኔስ ፡ ማን ፡ በዛለት

አዝ፦ ውለታው ፡ በዛ ፡ ጌታ ፡ ውለታው ፡ በዛ
ውለታው ፡ በዛ ፡ ኢየሱስ ፡ ውለታው ፡ በዛ (፪x)

አስታውሳለሁ ፡ ከምን ፡ እንዳነሳኝ
ሁሉም ፡ ሲጠየፍ ፡ እያየ ፡ ሲያልፈኝ
ቁስሌን ፡ ጠራርጐ ፡ እምባዬን ፡ ሲያብስ
አስቦ ፡ እኮ ፡ ነው ፡ እዚህ ፡ እንድደርስ

አዝ፦ ውለታው ፡ በዛ ፡ ጌታ ፡ ውለታው ፡ በዛ
ውለታው ፡ በዛ ፡ ኢየሱስ ፡ ውለታው ፡ በዛ (፪x)

አቤት ፡ እንደኔ ፡ ማንን ፡ ረዳህ
አቤት ፡ እንደኔ ፡ ማንን ፡ አገዝክ ፡ (አቤት ፡ አቤት ፡ አቤት)
አቤት ፡ ምህረትህ ፡ የገነነለት
አቤት ፡ እንደኔስ ፡ ማን ፡ በዛለት

አዝ፦ ውለታው ፡ በዛ ፡ ጌታ ፡ ውለታው ፡ በዛ ፡ (ውለታው)
ውለታው ፡ በዛ ፡ ኢየሱስ ፡ ውለታው ፡ በዛ (፪x)

ክብሬ ፡ ትዘምር ፡ ዝምም ፡ አትበል
ለቅሶዬን ፡ ለደስታ ፡ ጌታ ፡ ለውጧል
ማቄንም ፡ ቀዶ ፡ ደስታ ፡ አስታጠቀኝ
ምህረቱ ፡ በዝቶ ፡ በፊቱ ፡ አቆመኝ

ምህረቱ ፡ በዛ ፡ ጌታ ፡ ምህረቱ ፡ በዛ
ምህረቱ ፡ በዛ ፡ ኢየሱስ ፡ ምህረቱ ፡ በዛ
ጥበቃው ፡ በዛ ፡ ጌታ ፡ ጥበቃው ፡ በዛ
ጥበቃው ፡ በዛ ፡ ጌታ ፡ ጥበቃው ፡ በዛ
ሰላሙ ፡ በዛ ፡ ጌታ ፡ ሰላሙ ፡ በዛ
ሰላሙ ፡ በዛ ፡ ኢየሱስ ፡ ሰላሙ ፡ በዛ