ጠላት ፡ ተመቷል (Telat Temetual) - ዳግማዊ ፡ ጥላሁን

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ዳግማዊ ፡ ጥላሁን
(Dagmawi Tilahun)

Lyrics.jpg


(1)

ጌታ ፡ እርሱ ፡ ብቻ ፡ ነው
(Gieta Esu Becha New)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ ፯ (2004)
ቁጥር (Track):

(6)

ርዝመት (Len.): 5:24
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የዳግማዊ ፡ ጥላሁን ፡ አልበሞች
(Albums by Dagmawi Tilahun)

አዝ፦ እባብና ፡ ጊንጡን ፡ አስረግጦናል
በጠላት ፡ ኃይልም ፡ ላይ ፡ ሥልጣን ፡ ሰጥቶናል
የሰላም ፡ አምላክ ፡ እግራችን ፡ ሥር ፡ ቀጥቅጦታል
የሚያስቆመንም ፡ የለም ፡ ጠላት ፡ ተመቷል (፪x)

የጌታን ፡ ዕቃ ፡ ጦር ፡ እንለብሳለን
አይደል ፡ በደም ፡ ሥጋ ፡ መጋደላችን
የዲያቢሎስን ፡ ሽንገላ ፡ ተቃውመን
በአለቆች ፡ ስልጣናት ፡ ላይ ፡ እንዘምታለን

የሚንበለበለውን ፡ የክፉ ፡ ፍላፃ
እናጠፋዋለን ፡ አለን ፡ የእምነት ፡ ጋሻ

አዝ፦ እባብና ፡ ጊንጡን ፡ አስረግጦናል
በጠላት ፡ ኃይልም ፡ ላይ ፡ ሥልጣን ፡ ሰጥቶናል
የሰላም ፡ አምላክ ፡ እግራችን ፡ ሥር ፡ ቀጥቅጦታል
የሚያስቆመንም ፡ የለም ፡ ጠላት ፡ ተመቷል (፪x)

እርሱ ፡ ከኛ ፡ ጋር ፡ ነው ፡ ማን ፡ ይቃወመናል
በሕይወት ፡ ጐዳና ፡ ይኸው ፡ አራምዶናል
እጃችንን ፡ ይዞ ፡ መቼ ፡ ማድረስ ፡ ብቻ
በድል ፡ አሻግሮናል ፡ የሞትን ፡ ዳርቻ

እርሱ ፡ ኃይላችን ፡ ነው ፡ መመኪያ ፡ ክብራችን
መቼም ፡ አንወድቅም ፡ አለ ፡ ከጐናችን

አዝ፦ እባብና ፡ ጊንጡን ፡ አስረግጦናል
በጠላት ፡ ኃይልም ፡ ላይ ፡ ሥልጣን ፡ ሰጥቶናል
የሰላም ፡ አምላክ ፡ እግራችን ፡ ሥር ፡ ቀጥቅጦታል
የሚያስቆመንም ፡ የለም ፡ ጠላት ፡ ተመቷል (፪x)

በኃይል ፡ አይደለም ፡ በብርታት
የጠላት ፡ እንዲህ ፡ መመታት
በመንፈስ ፡ እንጂ ፡ በእግዚአብሔር
ክንዱን ፡ ተማምኖ ፡ በሚኖር (፬x)