ስለቴን ፡ ሁልጊዜ (Seletien Hulgizie) - ዳግማዊ ፡ ጥላሁን

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
ዳግማዊ ፡ ጥላሁን
(Dagmawi Tilahun)

Lyrics.jpg


(1)

ጌታ ፡ እርሱ ፡ ብቻ ፡ ነው
(Gieta Esu Becha New)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ ፯ (2004)
ቁጥር (Track):

(1)

ርዝመት (Len.): 5:27
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የዳግማዊ ፡ ጥላሁን ፡ አልበሞች
(Albums by Dagmawi Tilahun)

አዝ፦ ስለቴን ፡ ሁልጊዜ ፡ እፈጽማለሁ
ለሥምህ ፡ ዘላለም ፡ የእኔ ፡ ጌታ ፡ እዘምራለሁ (፪x)

በመከራዬ ፡ ጊዜ ፡ በአፌ ፡ የተናገርኩትን
ከአንደበቴም ፡ ያወጣሁትን ፡ ቃሌን
ይኸው ፡ እፈጽማለሁ ፡ ለአንተ ፡ ስለቴን (፪x)

አዝ፦ ስለቴን ፡ ሁልጊዜ ፡ እፈጽማለሁ
ለሥምህ ፡ ዘላለም ፡ የእኔ ፡ ጌታ ፡ እዘምራለሁ (፪x)

ጵኑ ግንብ፡ በጠላት ፡ ፊት ፡ ተስፋዬም ፡ ሆነኸኛልና
በድንኳንህ ፡ ለዘላለም ፡ እኖራለሁ
በክንፎችህ ፡ ጥላ ፡ እጋረዳለሁ (፪x)

አቤቱ ፡ አንተ ፡ ስለቴን ፡ ሰምተሃል
የልመናዬን ፡ ድምጽ ፡ ከላይ ፡ አድምጠሃል
ታዲያ ፡ የሰው ፡ ማዳን ፡ ከንቱ ፡ ነው ፡ ከንቱ ፡ ነው
ባገኘኝ ፡ መከራ ፡ ረዳቴ ፡ ጌታ ፡ ነው (፪x)

አዝ፦ ስለቴን ፡ ሁልጊዜ ፡ እፈጽማለሁ
ለሥምህ ፡ ዘላለም ፡ የእኔ ፡ ጌታ ፡ እዘምራለሁ (፫x)