ለእኔ ፡ የምታስበው (Lenie Yemetasebew) - ዳግማዊ ፡ ጥላሁን

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ዳግማዊ ፡ ጥላሁን
(Dagmawi Tilahun)

Lyrics.jpg


(1)

ጌታ ፡ እርሱ ፡ ብቻ ፡ ነው
(Gieta Esu Becha New)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ ፯ (2004)
ቁጥር (Track):

(4)

ርዝመት (Len.): 6:43
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የዳግማዊ ፡ ጥላሁን ፡ አልበሞች
(Albums by Dagmawi Tilahun)

አዝ፦ ለእኔ ፡ የምታስበው ፡ ይበልጣል
ለሰው ፡ የማይቻል ፡ ለአንተ ፡ ይቻላል
እኔ ፡ ዝም ፡ ብዬ ፡ እጠብቃለሁ
መታመኔን ፡ በአንተ ፡ አደርገዋለሁ

ጌታን ፡ እጠብቃለሁ ፡ አንተን ፡ እጠብቃለሁ (፪x)

የሳቁ ፡ ነበሩ ፡ በአንተ ፡ ስታመን
ትፈታዋለህ ፡ ስል ፡ እንቆቅልሼን
ጠላቴም ፡ ወዳጄም ፡ ስታስበኝ ፡ አዩ
የሚያመልከው ፡ አምላክ ፡ ለካ ፡ ይሰማል ፡ አሉ (፪x)

አዝ፦ ለእኔ ፡ የምታስበው ፡ ይበልጣል
ለሰው ፡ የማይቻል ፡ ለአንተ ፡ ይቻላል
እኔ ፡ ዝም ፡ ብዬ ፡ እጠብቃለሁ
መታመኔን ፡ በአንተ ፡ አደርገዋለሁ

ጌታን ፡ እጠብቃለሁ ፡ አንተን ፡ እጠብቃለሁ (፪x)

ቃልህን ፡ አምናለሁ ፡ አይደለም ፡ ስሜቴን
እንደምትሞላው ፡ መሻቴን ፡ የውስጤን
ፍፃሜና ፡ ተስፋ ፡ የምትሰጠዉ
ሃሳብህ ፡ ይበልጣል ፡ እጠብቃለሁ (፪x)

አዝ፦ ለእኔ ፡ የምታስበው ፡ ይበልጣል
ለሰው ፡ የማይቻል ፡ ለአንተ ፡ ይቻላል
እኔ ፡ ዝም ፡ ብዬ ፡ እጠብቃለሁ
መታመኔን ፡ በአንተ ፡ አደርገዋለሁ

ጌታን ፡ እጠብቃለሁ ፡ አንተን ፡ እጠብቃለሁ (፪x)

በአንተ ፡ እታመናለሁ ፡ አልነዋወጥም
ወደ ፡ ግራና ፡ ቀኝ ፡ አማራጭ ፡ አላይም
ግድ ፡ ይልሃልና ፡ ጌታ ፡ የእኔ ፡ ነገር
ከአንተ ፡ እጠብቃለሁ ፡ ወደሌላው ፡ ሳልዞር (፪x)

አንተን ፡ ብቻ ፡ እጠብቃለሁ
ከአንተ ፡ ወዴት ፡ እሄዳለሁ
የሕይወት ፡ ቃል ፡ አለህና
ለዘላለም ፡ የሚያጸና (፪x)