ጌታን ፡ እወደዋለሁ (Gietan Ewedewalehu) - ዳግማዊ ፡ ጥላሁን

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ዳግማዊ ፡ ጥላሁን
(Dagmawi Tilahun)

Lyrics.jpg


(1)

ጌታ ፡ እርሱ ፡ ብቻ ፡ ነው
(Gieta Esu Becha New)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ ፯ (2004)
ቁጥር (Track):

(8)

ርዝመት (Len.): 5:30
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የዳግማዊ ፡ ጥላሁን ፡ አልበሞች
(Albums by Dagmawi Tilahun)

የሰራኸውን ፡ ሳስተውለው ፡ ዞሬ
አልጨርሰውም ፡ ሁሉንም ፡ ዘርዝሬ
በፍቅር ፡ ቃላት ፡ እኔ ፡ ይህንን ፡ እላለሁ
የወደደኝን ፡ እኔም ፡ እወደዋለሁ

ጌታን ፡ እወደዋለሁ (፬x)

አዝ፦አንደበቴን ፡ ቀብቶታል
ጌታ ፡ ኑሮዬን ፡ ባርኮታል (፪x)
 
ታዲያ ፡ ምኑ ፡ ዝም ፡ ያሰኘኝ
ሁሌ ፡ ክብሩን ፡ እያሳየኝ (፪x)

ክበር ፡ ልበል ፡ ክበር ፡ እንጂ
ንገሥ ፡ ልበል ፡ ንገሥ ፡ እንጂ
ሌላ ፡ ቃላት ፡ ስለሌለኝ
ሾሜሃለው ፡ ንገስልኝ
 
ማነው ፡ የገመተ ፡ እዚህ ፡ ይደርሳል ፡ በሎ
ጠላት ፡ ያለውን ፡ ወሬ ፡ ተቀብሎ
ጌታ ፡ ሰው ፡ አረገኝ ፡ ጠላቴም ፡ አፈረ
ማቄንም ፡ ቀደደ ፡ ቀንበሬን ፡ ሰበረ

ጌታ ፡ ሰው ፡ አድርጐኛል (፬x)

አዝ፦አንደበቴን ፡ ቀብቶታል
ጌታ ፡ ኑሮዬን ፡ ባርኮታል (፪x)
 
ታዲያ ፡ ምኑ ፡ ዝም ፡ ያሰኘኝ
ሁሌ ፡ ክብሩን ፡ እያሳየኝ (፪x)

ክበር ፡ ልበል ፡ ክበር ፡ እንጂ
ንገሥ ፡ ልበል ፡ ንገሥ ፡ እንጂ
ሌላ ፡ ቃላት ፡ ስለሌለኝ
ሾሜሃለው ፡ ንገስልኝ
 
ባረከው ፡ ሕይወቴን ፡ ባረከው ፡ ኑሮዬን
ስሾመው ፡ በላዬ ፡ ሳመልከው ፡ ጌታዬን
በቀሪው ፡ ዘመኔም ፡ ጌታ ፡ ይንገስበት
በሰጠኝም ፡ ሕይወት ፡ እርሱ ፡ ይሰልጥንበት

ጌታን ፡ እሾመዋለሁ (፪x)
ጌታን ፡ አነግሰዋለሁ(፪x)
 
አዝ፦አንደበቴን ፡ ቀብቶታል
ጌታ ፡ ኑሮዬን ፡ ባርኮታል (፪x)
 
ታዲያ ፡ ምኑ ፡ ዝም ፡ ያሰኘኝ
ሁሌ ፡ ክብሩን ፡ እያሳየኝ (፪x)
 
ክበር ፡ ልበል ፡ ክበር ፡ እንጂ
ንገሥ ፡ ልበል ፡ ንገሥ ፡ እንጂ
ሌላ ፡ ቃላት ፡ ስለሌለኝ
ሾሜሃለው ፡ ንገስልኝ (፪x)