From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
በላይ ፡ በላይ ፡ በላይ ፡ በሰማይ
በታች ፡ በታች ፡ ሆነህ ፡ በምድር ላይ (፪x)
አዝ፦ ጌታ ፡ እርሱ ፡ ብቻ ፡ ነው (፪x)
ፍጥረት ፡ ወዶ ፡ ሚያመልከው
አምላክ ፡ እርሱ ፡ ብቻ ፡ ነው (፪x)
ፍጥረት ፡ ወዶ ፡ ሚያመልከው
ዛሬስ ፡ የታሉ ፡ ታላቅ ፡ ነን ፡ ያሉ
ዓመታት ፡ ሲያልፉ ፡ አብረው ፡ አለፉ
የሁሉ ፡ ገዢ ፡ የሁሉ ፡ የበላይ
የእኛ ፡ አምላክ ፡ ግን ፡ አለ ፡ በሰማይ (፭x)
አዝ፦ ጌታ ፡ እርሱ ፡ ብቻ ፡ ነው (፪x)
ፍጥረት ፡ ወዶ ፡ ሚያመልከው
አምላክ ፡ እርሱ ፡ ብቻ ፡ ነው (፪x)
ፍጥረት ፡ ወዶ ፡ ሚያመልከው
አላየሁኝም ፡ የሚመለክ ፡ እንደ ፡ እርሱ
አላየሁኝም ፡ የሚወደድ ፡ እንደ ፡ እርሱ
አልሰማሁኝም ፡ የሚመለክ ፡ እንደ ፡ እርሱ
አልሰማሁኝም ፡ የሚወደድ ፡ እንደ ፡ እርሱ
የምትወዱት ፡ ከእኔ ፡ ጋራ ፡ ተነሱ
የሚገባውን ፡ ክብር ፡ እንስጥ ፡ ለእርሱ (፪x)
በላይ ፡ በላይ ፡ በላይ ፡ በሰማይ
በታች ፡ በታች ፡ ሆነህ ፡ በምድር ላይ (፪x)
አዝ፦ ጌታ ፡ እርሱ ፡ ብቻ ፡ ነው (፪x)
ፍጥረት ፡ ወዶ ፡ ሚያመልከው
አምላክ ፡ እርሱ ፡ ብቻ ፡ ነው (፪x)
ፍጥረት ፡ ወዶ ፡ ሚያመልከው
የአህዛብ ፡ አማልክት ፡ የሚያመልኳቸው
የማይሰሙና ፡ ማያዩ ፡ ናቸው
ሰምቶ ፡ በእሳት ፡ የሚመልሰው
የምናመልከው ፡ እግዚአብሔር ፡ ብቻ ፡ ነው (፬x)
አዝ፦ ጌታ ፡ እርሱ ፡ ብቻ ፡ ነው (፪x)
ፍጥረት ፡ ወዶ ፡ ሚያመልከው
አምላክ ፡ እርሱ ፡ ብቻ ፡ ነው (፪x)
ፍጥረት ፡ ወዶ ፡ ሚያመልከው
ያለውና ፡ የነበረው ፡ የሚመጣው
ሁሌ ፡ ሁሉን ፡ የሚገዛ ፡ ጌታ ፡ አምላክ ፡ ነው
አልፋ ፡ እና ፡ ኦሜጋ ፡ እኔ ፡ ነኝ ፡ ብሏል
ወዶ ፡ ፈቅዶ ፡ ፍጥረትም ፡ ያመልከዋል (፪x)
ጌታ ፡ እርሱ ፡ ብቻ
አምላክ ፡ እርሱ ፡ ብቻ
ገዢ ፡ እርሱ ፡ ብቻ
ንጉሥ ፡ እርሱ ፡ ብቻ (፪x)
|