በዘመኔ ፡ ሁሉ (Bezemenie Hulu) - ዳግማዊ ፡ ጥላሁን

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ዳግማዊ ፡ ጥላሁን
(Dagmawi Tilahun)

Lyrics.jpg


(1)

ጌታ ፡ እርሱ ፡ ብቻ ፡ ነው
(Gieta Esu Becha New)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ ፯ (2004)
ቁጥር (Track):

፲ ፪ (12)

ርዝመት (Len.): 3:56
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የዳግማዊ ፡ ጥላሁን ፡ አልበሞች
(Albums by Dagmawi Tilahun)

“ሃሌሉያ ፡ ሃሌሉያ”

ሁልጊዜ ፡ እግዚአብሔርን ፡ እባርከዋለሁ
ምሥጋናው ፡ ዘወትር ፡ ዘወትር ፡ በአፌ ፡ ነው (፪x)

አቤቱ ፡ በኃይልህ ፡ ጌታ ፡ በችሎትህ
እዚህ ፡ ደርሻለው ፡ እስቲ ፡ ላመስግንህ (፪x)

ምሥጋና ፡ ምሥጋና ፡ ነው
ምሥጋና ፡ ምሥጋና ፡ ነው ፡ ያለው
ዝማሬ ፡ ዝማሬ ፡ ነው
ዝማሬ ፡ ዝማሬ ፡ ነው ፡ ያለው

በዘመኔ ፡ ሁሉ ፡ ላረክልኝ ፡ ነገር
ተመሥገን ፡ ሌላ ፡ እኔ ፡ ምን ፡ ልናገር (፪x)

ምሥጋና ፡ ምሥጋና ፡ ነው
ምሥጋና ፡ ምሥጋና ፡ ነው ፡ ያለው
ዝማሬ ፡ ዝማሬ ፡ ነው
ዝማሬ ፡ ዝማሬ ፡ ነው ፡ ያለው

ትዝታዬ ፡ እኮ ፡ ነህ ፡ በቀን ፡ በሌሊት
ቃሌም ፡ ንግግሬም ፡ ኢየሱስ ፡ ሆንክበት
ትዝታዬ ፡ እኮ ፡ ነህ ፡ በቀን ፡ በሌሊት
ቃሌም ፡ ንግግሬም ፡ ምሥጋና ፡ አለበት

አቤቱ ፡ በኃይልህ ፡ ጌታ ፡ በችሎትህ
እዚህ ፡ ደርሻለው ፡ እስቲ ፡ ላመስግንህ (፪x)

ይህች ፡ ቀን ፡ ናትና ፡ አንተ ፡ የሰራሃት
በሷ ፡ ደስ ፡ ይለኛል ፡ አደርጋለው ፡ ሀሴት (፪x)

አቤቱ ፡ በኃይልህ ፡ ጌታ ፡ በችሎትህ
እዚህ ፡ ደርሻለው ፡ እስቲ ፡ ላመስግንህ (፪x)

ምሥጋና ፡ ምሥጋና ፡ ነው
ምሥጋና ፡ ምሥጋና ፡ ነው ፡ ያለው
ዝማሬ ፡ ዝማሬ ፡ ነው
ዝማሬ ፡ ዝማሬ ፡ ነው ፡ ያለው