በችኮላ ፡ ከቶ ፡ አልወጣም (Bechekola Keto Alwetam) - ዳግማዊ ፡ ጥላሁን

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ዳግማዊ ፡ ጥላሁን
(Dagmawi Tilahun)

Lyrics.jpg


(1)

ጌታ ፡ እርሱ ፡ ብቻ ፡ ነው
(Gieta Esu Becha New)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ ፯ (2004)
ቁጥር (Track):

(5)

ርዝመት (Len.): 3:16
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የዳግማዊ ፡ ጥላሁን ፡ አልበሞች
(Albums by Dagmawi Tilahun)

በማስተዋል ፡ አደርጋለሁ
እረኛዬን ፡ እሰማዋለሁ
ያውቃል ፡ ከእኔ ፡ በብዙ ፡ ሺህ
ነፍሴ ፡ ይምራሽ ፡ አምላክሺ

ቀድሞ ፡ አይቶ ፡ የእኔን ፡ መንገድ
መራኝ ፡ በድንቅ ፡ በእርሱ ፡ ፈቃድ
ግራ ፡ ቀኜን ፡ ስላየልኝ
ተማምኜ ፡ እወጣለሁኝ

አዝ፦ በችኮላ ፡ ከቶ ፡ አልወጣም
በመኮብለል ፡ ደግሞ ፡ አልሄድም
እግዚአብሔር ፡ ይቀድመኛል
በፈቃዱ ፡ ይመራኛል (፪x)

በድንኳኔ ፡ እጠብቃለሁ
የአንተን ፡ ትእዛዝ ፡ እሰማለሁ
ውጣ ፡ ካልከኝ ፡ እወጣለሁ
ጠላቶቼን ፡ እመታለሁ

ጠላት ፡ ለእኔ ፡ ለሚያስበው
ግድም ፡ አይለኝ ፡ ስለሚለው
የእግዚአብሔር ፡ ኃይል ፡ ሸፍኖኛል
ደሙ ፡ እርሱ ፡ እኔን ፡ ስቦኛል

አዝ፦ በችኮላ ፡ ከቶ ፡ አልወጣም
በመኮብለል ፡ ደግሞ ፡ አልሄድም
እግዚአብሔር ፡ ይቀድመኛል
በፈቃዱ ፡ ይመራኛል (፪x)