አንተን ፡ ብቻ ፡ ሳስብ (Anten Becha Saseb) - ዳግማዊ ፡ ጥላሁን

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ዳግማዊ ፡ ጥላሁን
(Dagmawi Tilahun)

Lyrics.jpg


(1)

ጌታ ፡ እርሱ ፡ ብቻ ፡ ነው
(Gieta Esu Becha New)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ ፯ (2004)
ቁጥር (Track):

(2)

ርዝመት (Len.): 5:34
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የዳግማዊ ፡ ጥላሁን ፡ አልበሞች
(Albums by Dagmawi Tilahun)

መኖር ፡ አልችልም ፡ መዋል ፡ ማደር ፡ (አሃሃሃ)
አንተን ፡ ሳልጠራ ፡ ጌታ ፡ እግዚአብሔር ፡ (ኦሆሆሆ)
ፍቅር ፡ እኮ ፡ ነህ ፡ የማትጠገብ ፡ (አሃሃሃ)
ይረካል ፡ ልቤ ፡ ሁሌ ፡ አንተን ፡ ሲያስብ ፡ (ኦሆሆሆ)

አንተን ፡ ብቻ ፡ ሲያስብ ፡ አንተን ፡ ብቻ (፬x)

አያጓጓኝም ፡ ሌላው ፡ ነገር
ቢሆንልኝም ፡ ወይም ፡ ቢቀር
የምታረካኝ ፡ አንተ ፡ ብቻ ፡ ነህ
እጠግባለሁኝ ፡ ሁሌ ፡ ሳስብህ

አያጓጓኝም ፡ የዓለም ፡ ነገር
ቢሆንልኝም ፡ ወይም ፡ ቢቀር
የምታረካኝ ፡ አንተ ፡ ብቻ ፡ ነህ
እጠግባለሁኝ ፡ ሁሌ ፡ ሳስብህ

አንተን ፡ ብቻ ፡ ሳስብ ፡ አንተን ፡ ብቻ (፬x)

በአይምሮዬ ፡ የምስለዉ
በሕሊናዬ ፡ የማስበዉ
ሰላም ፡ የሚሰጠኝ ፡ አንድ ፡ ነገር
አንተን ፡ ማሰብ ፡ ነው ፡ እግዚአብሔር (፪x)

አንተን ፡ ብቻ ፡ ማሰብ ፡ አንተን ፡ ብቻ (፬x)

መኖር ፡ አልችልም ፡ መዋል ፡ ማደር ፡ (አሃሃሃ)
አንተን ፡ ሳልጠራ ፡ በዚች ፡ ምድር ፡ (ኦሆሆሆ)
ፍቅር ፡ እኮ ፡ ነህ ፡ የማትጠገብ ፡ (አሃሃሃ)
ይረካል ፡ ልቤ ፡ ሁሌ ፡ አንተን ፡ ሲያስብ ፡ (ኦሆሆሆ)

አንተን ፡ ብቻ ፡ ሲያስብ ፡ አንተን ፡ ብቻ (፬x)

ፍቅር ፡ የያዘኝ ፡ ከኢየሱስ ፡ ነዉ
መች ፡ ከሚጠፋ ፡ ከሚያልፈዉ
ምኞቴ ፡ የሆንክ ፡ አገኘሁህ
አንተኑ ፡ ሳስብ ፡ አረፍኩብህ

ፍቅር ፡ የያዘኝ ፡ ከጌታዬ ፡ ነዉ
መች ፡ ከሚጠፋ ፡ ከሚያልፈዉ
ምኞቴ ፡ የሆንክ ፡ አገኘሁህ
አንተኑ ፡ ሳስብ ፡ አረፍኩብህ

አንተን ፡ ብቻ ፡ ሳስብ ፡ አንተን ፡ ብቻ (፪x)

አንተን ፡ ብቻ ፡ ሳመልክ ፡ አንተን ፡ ብቻ
አንተን ፡ ብቻ ፡ ሳከብር ፡ አንተን ፡ ብቻ (፪x)