From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
አዝ: አመሰግናለሁ ፡ አመሰግናለሁኝ ፡ አመሰግናለሁ (፪x)
ፍቅሩ ፡ ልቤን ፡ ተናገረው
እንዲያመልከው ፡ አነሳሳው
ሥራው ፡ ልቤን ፡ ተናገረው
እንዲያመልከው ፡ አነሳሳው
አመሰግናለሁ ፡ አመሰግናለሁኝ ፡ አመሰግናለሁ (፪x)
ዘወትር ፡ ማለዳ ፡ ቀንና ፡ ሌሊቱ
እያልኩኝ ፡ አልፋለሁ ፡ አቤት ፡ ምህረቱ
ከመቅደሱ ፡ ሆኖ ፡ እርሱም ፡ ይሰማኛል
እኔስ ፡ ምሥጋናዬ ፡ በእርሱ ፡ ዘንድ ፡ ተወዷል
አዝ: ፍቅሩ ፡ ልቤን ፡ ተናገረው
እንዲያመልከው ፡ አነሳሳው
ሥራው ፡ ልቤን ፡ ተናገረው
እንዲያመልከው ፡ አነሳሳው
አመሰግናለሁ ፡ አመሰግናለሁኝ ፡ አመሰግናለሁ (፪x)
ቃላቶች ፡ ሳይወጡ ፡ የሚጐተጉቱ
አመስግነኝ ፡ ብሎ ፡ ጌታስ ፡ በአንደበቱ
ስራ ፡ እና ፡ ፍቅሩ ፡ መች ፡ ያስቀምጠኛል
ልቤስ ፡ በፈቃዱ ፡ ላመስግነው ፡ ብሏል
አዝ: ፍቅሩ ፡ ልቤን ፡ ተናገረው
እንዲያመልከው ፡ አነሳሳው
ሥራው ፡ ልቤን ፡ ተናገረው
እንዲያመልከው ፡ አነሳሳው
አመሰግናለሁ ፡ አመሰግናለሁኝ ፡ አመሰግናለሁ (፪x)
ልቤ ፡ አሰበ ፡ ፍቅሩን
እጅግ ፡ መወደዱን
ተነሳ ፡ ለአምልኮ
ጌታውን ፡ ፈልጐ (፪x)
ነፍሴ ፡ ታዳጊዋን ፡ ታመሰግናለች
ከአዳኞች ፡ ወጥመድ ፡ ድኛለው ፡ ትላለች
በፀናችው ፡ ክንዱ ፡ እግዚአብሔር ፡ ታድጐ
የራሱ ፡ አድርጐኛል ፡ ምሥጋናን ፡ ፈልጐ
አዝ: ፍቅሩ ፡ ልቤን ፡ ተናገረው
እንዲያመልከው ፡ አነሳሳው
ሥራው ፡ ልቤን ፡ ተናገረው
እንዲያመልከው ፡ አነሳሳው
አመሰግናለሁ ፡ አመሰግናለሁኝ ፡ አመሰግናለሁ (፪x)
ልቤ ፡ አሰበ ፡ ፍቅሩን
እጅግ ፡ መወደዱን
ተነሳ ፡ ለአምልኮ
ጌታውን ፡ ፈልጐ (፪x)
አመሰግናለሁ ፡ አመሰግናለሁኝ ፡ አመሰግናለሁ
|