From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
እንዴት ፡ ልርሳህ ፡ እንዴት ፡ ችዬ
ፍቅርህ ፡ ብዙ ፡ ነው ፡ ጌታዬ (፪x)
አዝ፦ የእኔ ፡ ጌታ ፡ እወድሃለሁ
በአንተ ፡ ብርታት ፡ ሰው ፡ ሆኛለሁ
በከበረው ፡ ሠረገላ
ያስቀመጠኝ/ያሰበኝም ፡ የለም ፡ ከአንተ ፡ ሌላ (፪x)
መማለጃ ፡ አትፈልግ ፡ እጅ ፡ መንሻ
ለምህረትህ ፡ የለህ ፡ መጨረሻ
እንዲያው ፡ ወደኸኝ ፡ ነው ፡ ወግ ፡ ያየሁት
በከፍታ ፡ ስፍራ ፡ የወጣሁት (፪x)
አዝ፦የእኔ ፡ ጌታ ፡ (የእኔ ፡ ጌታ) ፡ እወድሃለሁ ፡ (እወድሃለሁ)
በአንተ ፡ ብርታት ፡ ሰው ፡ ሆኛለሁ
በከበረው ፡ (በከበረው) ፡ ሠረገላ ፡ (ሠረገላ)
ያስቀመጠኝ ፡ የለም ፡ ከአንተ ፡ ሌላ
ምክንያት ፡ ሰበብ ፡ ፈላልጌ
ልሰዋለት ፡ ለአምላኬ (፪x)
አዝ፦የእኔ ፡ ጌታ ፡ (የእኔ ፡ ጌታ) ፡ እወድሃለሁ ፡ (እወድሃለሁ)
በአንተ ፡ ብርታት ፡ ሰው ፡ ሆኛለሁ
በከበረው ፡ (በከበረው) ፡ ሠረገላ ፡ (ሠረገላ)
ያስቀመጠኝ/ያሰበኝም ፡ የለም ፡ ከአንተ ፡ ሌላ (፪x)
ከመኳንንት ፡ ጋራ ፡ አስቀመጥከኝ
የክብርህን ፡ ዙፋን ፡ አወረስከኝ
ምንም ፡ የለም ፡ ለኔ ፡ ያላረከው
ከነገሮች ፡ በላይ ፡ እወድሃለው (፪x)
አዝ፦የእኔ ፡ ጌታ ፡ (የእኔ ፡ ጌታ) ፡ እወድሃለሁ ፡ (እወድሃለሁ)
በአንተ ፡ ብርታት ፡ ሰው ፡ ሆኛለሁ
በከበረው ፡ (በከበረው) ፡ ሠረገላ ፡ (ሠረገላ)
ያስቀመጠኝ/ያሰበኝም ፡ የለም ፡ ከአንተ ፡ ሌላ (፪x)
|