ጌታ ፡ አለ ፡ ከጐኔ (Gieta Ale Kegonie) - ዳግማዊ ፡ ጥላሁን

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ዳግማዊ ፡ ጥላሁን
(Dagmawi Tilahun)

Dagmawi Tilahun 2.jpg


(2)

ጌታ ፡ አለ ፡ ከጐኔ
(Gieta Ale Kegonie)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ ፯ (2004)
ቁጥር (Track):

(3)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የዳግማዊ ፡ ጥላሁን ፡ አልበሞች
(Albums by Dagmawi Tilahun)

ሲሰማ ፡ ፉከራው ፡ ሽለላው ፡ የጠላቴ ፡ ወሬ
(አሃሃ) ፡ የጠላቴ ፡ ወሬ (፪x)
ሰው ፡ የሚተርፍ ፡ አይመስልም ፡ እኔ ፡ ግን ፡ አለሁ ፡ እስከዛሬ
(አሃሃ) ፡ አለሁ ፡ እስከዛሬ (፪x)
ተዉኝ ፡ ሌላ ፡ አልሰማም ፡ ቢፎክር ፡ ሁሉም ፡ ለጊዜው ፡ ነው
(አሃሃ) ፡ ሁሉም ፡ ለጊዜው ፡ ነው (፪x)
የሚያስፈራም ፡ ሆነ ፡ የሚያስደነግጠው ፡ እግዚአብሔር ፡ ብቻ ፡ ነው
(አሃሃ) ፡ እግዚአብሔር ፡ ብቻ ፡ ነው (፪x)

ያረገውን ፡ አስቤ ፡ ከልቤ ፡ ኦ ፡ ከልቤ
ማደሪያው ፡ ዙፋኑን ፡ ከብቤ ፡ ኦ ፡ ከብቤ
ምሥጋና ፡ አምልኮ ፡ እላለሁ
እኔማ ፡ መች ፡ ጠገብኩ ፡ ረካሁ (፪x)

አለኝ ፡ ብዙ ፡ ሥራ ፡ ልነሳ ፡ ተረኛ ፡ ነኝ ፡ እኔ
(አሃሃ) ፡ ተረኛ ፡ ነኝ ፡ እኔ (፪x)
አትበሉ ፡ የልጅ ፡ ነገር ፡ እዩ ፡ እንጂ ፡ ጌታ ፡ አለ ፡ ከጐኔ
(አሃሃ) ፡ ጌታ ፡ አለ ፡ ከጐኔ (፪x)
የሚመችም ፡ ባይሆን ፡ ቢከፋ ፡ ቢበዛም ፡ ውጊያዉ
(አሃሃ)፡ ቢበዛም ፡ ውጊያዉ (፪x)
እኔ ፡ አልመለስም ፡ ፈርቼ ፡ ጌታን ፡ ይዣለሁ
(አሃሃ) ፡ ጌታን ፡ ይዣለሁ (፪x)

ያረገውን ፡ አስቤ ፡ ከልቤ ፡ ኦ ፡ ከልቤ
ማደሪያው ፡ ዙፋኑን ፡ ከብቤ ፡ ኦ ፡ ከብቤ
ምሥጋና ፡ አምልኮ ፡ እላለሁ
እኔማ ፡ መች ፡ ጠገብኩ ፡ ረካሁ
ምሥጋና ፡ አምልኮ ፡ እላለሁ
ለኔማ ፡ ብዙ ፡ ነው ፡ የሆንከው

የክብሩ ፡ ደመና ፡ መንፈሱ ፡ በላዬ ፡ አለፈ
(አሃሃ)፡ በላዬ ፡ አለፈ (፪x)
ጓዙን ፡ ጠቀለለ ፡ ሃዘኔ ፡ ባንተ ፡ ተገፈፈ
(አሃሃ) ፡ ባንተ ፡ ተገፈፈ (፪x)
የሰማዩ ፡ አዋጅ ፡ ዜናው ፡ ለኔ ፡ ምስራች ፡ ነው
(አሃሃ) ፡ ለኔ ፡ ምስራች ፡ ነው (፪x)
ምንም ፡ ነገር ፡ ባይኖር ፡ አምላኬ ፡ ከበቂ ፡ በላይ ፡ ነው
(አሃሃ) ፡ ከበቂ ፡ በላይ ፡ ነው (፪x)

ያረገውን ፡ አስቤ ፡ ከልቤ ፡ ኦ ፡ ከልቤ
ማደሪያውን ፡ ዙፋኑን ፡ ከብቤ ፡ ኦ ፡ ከብቤ

ምሥጋና ፡ አምልኮ ፡ እላለሁ
እኔማ ፡ መች ፡ ጠገብኩ ፡ ረካሁ (፪x)

ምሥጋና ፡ አምልኮ ፡ እላለሁ
ለኔማ ፡ ብዙ ፡ ነው ፡ የሆንከው (፪x)