ኢየሱስ ፡ የዘላለም ፡ ንጉሥ (Eyesus Yezelalem Negus) - ዳግማዊ ፡ ጥላሁን

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ዳግማዊ ፡ ጥላሁን
(Dagmawi Tilahun)

Dagmawi Tilahun 2.jpg


(2)

ጌታ ፡ አለ ፡ ከጐኔ
(Gieta Ale Kegonie)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ ፯ (2004)
ቁጥር (Track):

፲ ፪ (12)

ርዝመት (Len.): 6:25
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የዳግማዊ ፡ ጥላሁን ፡ አልበሞች
(Albums by Dagmawi Tilahun)

ኢየሱስ ፡ የዘላለም ፡ ንጉሥ
ኢየሱስ ፡ እንከን ፡ የለህ ፡ ቅዱስ
ኢየሱስ ፡ የማምለጫ ፡ አለቴ
ኢየሱስ ፡ በአንተ ፡ ነው ፡ እረፍቴ (፪x)

አመልከዋለሁ ፡ ሁልጊዜ
ቤዛ ፡ ሆኗታል ፡ ለነፍሴ (፪x)

ኢየሱሴ ፡ አዳኝ ፡ ንጉሤ
ኢየሱሴ ፡ ቤዛ ፡ ለነፍሴ
ኢየሱሴ ፡ አዳኝ ፡ ለነፍሴ
ኢየሱሴ ፡ ቤዛ ፡ ንጉሤ

ቸርነትህን ፡ ላውራ ፡ ልናገረው ፡ እንጂ
እንዴት ፡ እኖራለሁ ፡ ከምህረትህ ፡ ውጪ
መዳኔም ፡ በአንተ ፡ ነው ፡ ማምለጤም ፡ መትረፌ
ቁስሌም ፡ የሻረልኝ ፡ አንተን ፡ ተደግፌ

አመልከዋለሁ ፡ ሁልጊዜ
ቤዛ ፡ ሆኗታል ፡ ለነፍሴ (፪x)

ኢየሱሴ ፡ አዳኝ ፡ ንጉሤ
ኢየሱሴ ፡ ቤዛ ፡ ለነፍሴ
ኢየሱሴ ፡ አዳኝ ፡ ለነፍሴ
ኢየሱሴ ፡ ቤዛ ፡ ንጉሤ

ሰልፍማ ፡ በዝቶ ፡ እንዳልተጨነኩ
ድምጽህን ፡ ስሰማ ፡ በቃልህ ፡ አረፍኩ
ሰላሜ ፡ አንተው ፡ ነህ ፡ የእረፍቴ ፡ ምንጭ
ወዳጅ ፡ አላውቅም ፡ እኔስ ፡ ከአንተ ፡ ውጭ (፪x)

ከአንተ ፡ ውጭ ፡ ወዳጅ ፡ አላውቅም
ከአንተ ፡ ውጭ ፡ አጋዥ ፡ አላውቅም
ከአንተ ፡ ውጭ ፡ ሰላም ፡ አላውቅም
ከአንተ ፡ ውጭ ፡ ወዳጅ ፡ አላውቅም

አመልከዋለሁ ፡ ሁልጊዜ
ቤዛ ፡ ሆኗታል ፡ ለነፍሴ (፪x)

ኢየሱሴ ፡ አዳኝ ፡ ንጉሤ
ኢየሱሴ ፡ ቤዛ ፡ ለነፍሴ
ኢየሱሴ ፡ አዳኝ ፡ ለነፍሴ
ኢየሱሴ ፡ ቤዛ ፡ ንጉሤ

ቸርነትህን ፡ ላውራ ፡ ልናገረው ፡ እንጂ
እንዴት ፡ እኖራለሁ ፡ ከምህረትህ ፡ ውጪ
መዳኔም ፡ በአንተ ፡ ነው ፡ ማምለጤም ፡ መትረፌ
ቁስሌም ፡ የሻረልኝ ፡ አንተን ፡ ተደግፌ