አምላኬ ፡ የኔማ ተስፋ (Amelka yenama tesfa) - ዳግማዊ ፡ ጥላሁን

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ዳግማዊ ፡ ጥላሁን
(Dagmawi Tilahun)

Dagmawi Tilahun 2.jpg


(2)

ጌታ ፡ አለ ፡ ከጐኔ
(Gieta Ale Kegonie)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ ፯ (2004)
ቁጥር (Track):

(10)

ርዝመት (Len.): 4:47
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የዳግማዊ ፡ ጥላሁን ፡ አልበሞች
(Albums by Dagmawi Tilahun)

ሰው ፡ አይሆንም ፡ ብለው ፡ ሰው ፡ አረገኝ ፡ ጌታ ፡ (ጌታዬ ፡ ጌታ ፡ ጌታዬ)
ደጀን ፡ የለው ፡ ብለው ፡ ሆነልኝ ፡ መከታ ፡ (ጌታዬ ፡ ጌታ ፡ ጌታዬ)
እንዳሰቡት ፡ ሳይሆን ፡ እንዳሰበልኝ ፡ ነው ፡ (ጌታዬ ፡ ጌታ ፡ ጌታዬ)
ገና ፡ መቼ ፡ አዩ ፡ ይሄ ፡ ጅማሬ ፡ ነው ፡ (ጌታዬ ፡ ጌታ ፡ ጌታዬ)

አምላኬ ፡ የኔማ ፡ ተስፋ
እንዳልወድቅ ፡ ከቶ ፡ እንዳልጠፋ
የእኔ ፡ አባት ፡ የእኔ ፡ መድኃኒት
በአንተ ፡ ነው ፡ እዚህ ፡ የደረስኩት

አንተ ፡ ነህ ፡ የኔማ ፡ ተስፋ
እንዳልወድቅ ፡ ከቶ ፡ እንዳልጠፋ
የእኔ ፡ አባት ፡ የእኔ ፡ መድኃኒት
በአንተ ፡ ነው ፡ እዚህ ፡ የደረስኩት

በአንተ ፡ ነው ፡ እዚህ ፡ የደረስኩት
በአንተ ፡ ነው ፡ ሁሉን ፡ ያለፍኩት
በአንተ ፡ ነው ፡ ቀን ፡ የወጣልኝ
ጌታዬ ፡ ተመስገንልኝ (፪x)

አስታዋሽ ፡ ለሌለኝ ፡ ለተረሳሁ ፡ በሰው ፡ (ጌታዬ ፡ ጌታ ፡ ጌታዬ)
ከተፍ ፡ ብሎልኛል ፡ ፍቅሩ ፡ በተግባር ፡ ነው ፡ (ጌታዬ ፡ ጌታ ፡ ጌታዬ)
እንባ ፡ ያወጡ ፡ አይኖቼ ፡ በደስታ ፡ ተሞሉ ፡ (ጌታዬ ፡ ጌታ ፡ ጌታዬ)
ህመሜኮ ፡ ያመዋል ፡ ስለሆንኩ ፡ አካሉ ፡ (ጌታዬ ፡ ጌታ ፡ ጌታዬ)

አምላኬ ፡ የኔማ ፡ ተስፋ
እንዳልወድቅ ፡ ከቶ ፡ እንዳልጠፋ
የእኔ ፡ አባት ፡ የእኔ ፡ መድኃኒት
በአንተ ፡ ነው ፡ እዚህ ፡ የደረስኩት

አንተ ፡ ነህ ፡ የኔማ ፡ ተስፋ
እንዳልወድቅ ፡ ከቶ ፡ እንዳልጠፋ
የእኔ ፡ አባት ፡ የእኔ ፡ መድኃኒት
በአንተ ፡ ነው ፡ እዚህ ፡ የደረስኩት

በአንተ ፡ ነው ፡ እዚህ ፡ የደረስኩት
በአንተ ፡ ነው ፡ ሁሉን ፡ ያለፍኩት
በአንተ ፡ ነው ፡ ቀን ፡ የወጣልኝ
ጌታዬ ፡ ተመስገንልኝ (፪x)

የምስኪኑ ፡ ወዳጅ ፡ ለተከፋው ፡ ፈራጅ
ለድሃደጉ ፡ አባት ፡ ለደከመው ፡ ብርታት (፪x)

ማረፊያ ፡ ጥላዬ
መጠጊያ ፡ ከለላዬ
ኢየሱስ ፡ ጌታዬ (፪x)

ኢየሱስ ፡ ጌታዬ (፬x)