ትቼልሃለሁ (Techielehalehu) - ዳግማዊ ፡ ጥላሁን

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ዳግማዊ ፡ ጥላሁን
(Dagmawi Tilahun)

Dagmawi Tilahun 3.jpg


(3)

ፍቅር ፡ ይቅር ፡ ያለው
(Feqer Yeqer Yalew)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፩ (2009)
ቁጥር (Track):

(7)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የዳግማዊ ፡ ጥላሁን ፡ አልበሞች
(Albums by Dagmawi Tilahun)

ግራ ፡ ሲገባኝ ፡ ሌላን ፡ አይቼ
እርፍ ፡ እላለሁ ፡ ለአንተ ፡ ሰጥቼ
ግራ ፡ ሲገባኝ ፡ ሁኔታ ፡ አይቼ
እርፍ ፡ እላለሁ ፡ በአንተ ፡ ላይ ፡ ትቼ

አዝ፦ትቼልሃለሁ ፡ ጌታዬ ፡ ትቼልሃለሁ (፪x)
ትቼልሃለሁ ፡ ከእንግዲህ ፡ ትቼልሃለሁ (፪x)

በአንተ ፡ ላይ ፡ ነገሬን ፡ ትቼ
በአንተ ፡ ላይ ፡ አምኜ ፡ ወጥቼ
በአንተ ፡ ላይ ፡ አፍሬ ፡ አላውቅም
በአንተ ፡ ላይ ፡ በአንተ ፡ ኮርቼ (፪x)

አይጥልማ ፡ አይረሳማ ፡ የእኔ ፡ ጌታ
አልናወጥ ፡ በሚሰማ ፡ በሁኔታ (፪x)

ከንጉሥ ፡ ተስፋ ፡ ከአለቆች ፡ ቃል
ነፍስ ፡ መንፈሴ ፡ አንተን ፡ አምኖሃል
ባያምኑህ ፡ እንኳን ፡ ታምነህ ፡ የምትኖር
ትቼልሃለሁ ፡ ጌታ ፡ የእኔን ፡ ነገር (፪x)

አዝ፦ትቼልሃለሁ ፡ ጌታዬ ፡ ትቼልሃለሁ (፪x)
ትቼልሃለሁ ፡ ከእንግዲህ ፡ ትቼልሃለሁ (፪x)

ግራ ፡ ሲገባኝ ፡ ሌላን ፡ አይቼ
እርፍ ፡ እላለሁ ፡ ለአንተ ፡ ሰጥቼ
ግራ ፡ ሲገባኝ ፡ ሁኔታ ፡ አይቼ
እርፍ ፡ እላለሁ ፡ በአንተ ፡ ላይ ፡ ትቼ

አዝ፦ትቼልሃለሁ ፡ ጌታዬ ፡ ትቼልሃለሁ (፪x)
ትቼልሃለሁ ፡ ከእንግዲህ ፡ ትቼልሃለሁ (፪x)

የተናገረኝ ፡ ያየልኝ ፡ ያኔ
ይሆናል ፡ አመንኩ ፡ ሳላየው ፡ በዓይኔ
ገመዴ ፡ ወድቃ ፡ ባማረ ፡ ስልፍራ
አልገባም ፡ እኔስ ፡ በአምላኬ ፡ ስራ (፪x)

አይጥልማ ፡ አይረሳማ ፡ የእኔ ፡ ጌታ
አልናወጥ ፡ በሚሰማ ፡ በሁኔታ (፪x)

በአንተ ፡ ላይ ፡ ነገሬን ፡ ትቼ ፡ በአንተ ፡ ላይ ፡ አምኜ ፡ ወጥቼ
በአንተ ፡ ላይ ፡ አፍሬ ፡ አላውቅም ፡ በአንተ ፡ ላይ ፡ በአንተ ፡ ኮርቼ
ነገሬን ፡ ነገሬን ፡ ትቼ ፡ አምኜ ፡ አምኜ ፡ ወጥቼ
አፍሬ ፡ አፍሬ ፡ አላውቅም ፡ በአንተማ ፡ በአንተ ፡ ኮርቼ

አይጥልማ ፡ አይረሳማ ፡ የእኔ ፡ ጌታ
አልናወጥ ፡ በሚሰማ ፡ በሁኔታ (፪x)

አዝ፦ትቼልሃለሁ ፡ ጌታዬ ፡ ትቼልሃለሁ (፪x)
ትቼልሃለሁ ፡ ከእንግዲህ ፡ ትቼልሃለሁ (፪x)