አቻ ፡ አልተገኘልህም (Title) - ዳግማዊ ፡ ጥላሁን

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ዳግማዊ ፡ ጥላሁን
(Dagmawi Tilahun)

Dagmawi Tilahun 3.jpg


(3)

ፍቅር ፡ ይቅር ፡ ያለው
(Feqer Yeqer Yalew)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፩ (2009)
ቁጥር (Track):

(1)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የዳግማዊ ፡ ጥላሁን ፡ አልበሞች
(Albums by Dagmawi Tilahun)

ሳመልክህ ፡ እንድኖር ፡ ውስጤ ፡ ሳይል ፡ ዝም
ምነው ፡ ቀኑ ፡ ባይኖር ፡ ሌቱም ፡ ባይጨልም
መንፈሱን ፡ ፈልጌ ፡ ተዘልዬ ፡ እኔማ
ሰከንዷም ፡ አትለፍ ፡ ድምጼ ፡ ሳይሰማ (፪x)

አዝ፦ እኔማ ፡ እንዴት ፡ ችዬ ፡ ዝም
እኔማ ፡ አምልኮዬ ፡ አይቆም (፪x)

ጌታዬ ፡ መጣና ፡ እንባዬን ፡ አየና
ነገሬን ፡ ፈወሰው ፡ የልቤ ፡ ደርሰ
አይደለም ፡ ከሩቅ ፡ አለሁ ፡ ባዬ
እንዲህ ፡ ነው ፡ ሲሰራ ፡ ጌታዬ (፪x)

እንዳሰብኩት ፡ ባይሆን ፡ (ይሁና ፡ አዋቂ ፡ ነውና)
የልቤ ፡ ባይሞላ ፡ (ይሁና ፡ አዋቂ ፡ ነውና)
መልሴ ፡ ቢዘገይም ፡ (ይሁና ፡ አዋቂ ፡ ነውና)
ቅትር ፡ ላይ ፡ ቢጨልም ፡ (ይሁና ፡ አዋቂ ፡ ነውና)

ምክንያቴን ፡ ጥዬ ፡ ሰበቤን ፡ ትቼ
አመልካለሁኝ ፡ አምላክ ፡ አግኝቼ (፪x)

ሳመልክህ ፡ እንድኖር ፡ ውስጤ ፡ ሳይል ፡ ዝም
ምነው ፡ ቀኑ ፡ ባይኖር ፡ ሌቱም ፡ ባይጨልም
መንፈሱን ፡ ፈልጌ ፡ ተዘልዬ ፡ እኔማ
ሰከንዷም ፡ አትለፍ ፡ ድምጼ ፡ ሳይሰማ (፪x)

አዝ፦ እኔማ ፡ እንዴት ፡ ችዬ ፡ ዝም
እኔማ ፡ አምልኮዬ ፡ አይቆም (፪x)

እረስቶታል ፡ አሉ ፡ (ይበሉ ፡ ይፈጸማል ፡ ቃሉ)
አባትነቱ ፡ የታል ፡ (ይበሉ ፡ ይፈጸማል ፡ ቃሉ)
ህልሜን ፡ ህልም ፡ ቢሉት ፡ (ይበሉ ፡ ይፈጸማል ፡ ቃሉ)
ሆኖ ፡ እስከሚያዩት ፡ (ይበሉ ፡ ይፈጸማል ፡ ቃሉ)

ምክንያቴን ፡ ጥዬ ፡ ሰበቤን ፡ ትቼ
አመልካለሁኝ ፡ አምላክ ፡ አግኝቼ (፪x)

ኢየሱሴ ፡ መጣና ፡ እንባዬን ፡ አየና
ነገሬን ፡ ፈወሰው ፡ የልቤ ፡ ደርሰ
አይደለም ፡ ከሩቅ ፡ አለሁ ፡ ባዬ
እንዲህ ፡ ነው ፡ ሲሰራ ፡ ጌታዬ (፪x)

አዝ፦ እኔማ ፡ እንዴት ፡ ችዬ ፡ ዝም
እኔማ ፡ አምልኮዬ ፡ አይቆም (፪x)