ልበልህ ፡ አለኝታዬ (Lebeleh Alegntayie) - ዳግማዊ ፡ ጥላሁን

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ዳግማዊ ፡ ጥላሁን
(Dagmawi Tilahun)

Dagmawi Tilahun 3.jpg


(3)

ፍቅር ፡ ይቅር ፡ ያለው
(Feqer Yeqer Yalew)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፩ (2009)
ቁጥር (Track):

(5)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የዳግማዊ ፡ ጥላሁን ፡ አልበሞች
(Albums by Dagmawi Tilahun)

አምላኬ ፡ ሆይ ፡ የእኔ ፡ አለኝታ ፡ የሞትክልኝ ፡ በእኔ ፡ ቦታ
አምላኬ ፡ ሆይ ፡ የእኔ ፡ አለኝታ ፡ የቆምክልኝ ፡ በእኔ ፡ ቦታ

(ኧኸ) ፡ ጅማሬዬ ፡ ላይ ፡ (ኧኸ) ፡ ታሪክ ፡ ሲዘጉ
(ኧኸ) ፡ ቁጣህ ፡ ነደደ ፡ (ኧኸ) ፡ አንተን ፡ እንደነኩ
(ኧኸ) ፡ ወጪ ፡ ወራጁ ፡ (ኧኸ) ፡ የሚቀናበት
(ኧኸ) ፡ ክብርህ ፡ ፈሰሰ ፡ (ኧኸ) ፡ ገባ ፡ ከእኔ ፡ ቤት

አዝ፦ ልበልህ ፡ (ልበልህ) ፡ አለኝታዬ ፡ (አለኝታዬ)
ልበልህ ፡ (ልበልህ) ፡ ከለላዬ ፡ (ከለላዬ) (፪x)

(ኧኸ) ፡ ሲማማምሉና ፡ (ኧኸ) ፡ ሲማከሩብኝ
(ኧኸ) ፡ ፍላጻህ ፡ ወርዶ ፡ (ኧኸ) ፡ አፈረሰልኝ
(ኧኸ) ፡ በጠላት ፡ ቀዬ ፡ (ኧኸ) ፡ በጠላት ፡ መንደር
(ኧኸ) ፡ ስለአለኝታዬ ፡ (ኧኸ) ፡ እስኪ ፡ ልዘምር

አዝ፦ ልበልህ ፡ (ልበልህ) ፡ አለኝታዬ ፡ (አለኝታዬ)
ልበልህ ፡ (ልበልህ) ፡ ከለላዬ ፡ (ከለላዬ) (፪x)

ጠላቴ ፡ ብዙ ፡ ለፍቶ ፡ በእጁ ፡ ሊያስገባኝ ፡ ጓግቶ
ፍቅርህ ፡ ያሰረው ፡ ልቤ ፡ አንተን ፡ አለኝ ፡ ሀሳቤ (፪x)

አምላኬ ፡ ሆይ ፡ የእኔ ፡ አለኝታ ፡ የሞትክልኝ ፡ በእኔ ፡ ቦታ
አምላኬ ፡ ሆይ ፡ የእኔ ፡ አለኝታ ፡ የቆምክልኝ ፡ በእኔ ፡ ቦታ

(ኧኸ) ፡ ማለዳ ፡ ቀትር ፡ (ኧኸ) ፡ ነግቶ ፡ እስኪመሽ
(ኧኸ) ፡ በእኔ ፡ ዝማሬ ፡ (ኧኸ) ፡ ጠላት ፡ ሲረበሽ
(ኧኸ) ፡ የማታው ፡ ለቅሶ ፡ (ኧኸ) ፡ ጠዋት ደስታ
(ኧኸ) ፡ እንዲህ ፡ ነው ፡ እንጂ ፡ (ኧኸ) ፡ ማረፍ ፡ በጌታ

አዝ፦ ልበልህ ፡ (ልበልህ) ፡ አለኝታዬ ፡ (አለኝታዬ)
ልበልህ ፡ (ልበልህ) ፡ ከለላዬ ፡ (ከለላዬ) (፪x)

ጥቃቴን ፡ ከላይ ፡ አይተህ ፡ ክብርህን ፡ ለእኔ ፡ ትተህ
ወርደህ ፡ ያወጣኸኝ ፡ ሞተህ ፡ ያተረፍከኝ (፪x)

አዝ፦ ልበልህ ፡ (ልበልህ) ፡ አለኝታዬ ፡ (አለኝታዬ)
ልበልህ ፡ (ልበልህ) ፡ ከለላዬ ፡ (ከለላዬ) (፫x)