From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዙሪያዬን ፡ ሳይ ፡ ለመዳኔ ፡ ሰው ፡ የለኝም ፡ አንድ ፡ ለእኔ
ሰድበኸው ፡ ሙት ፡ አትበሉኝ ፡ ለእኔው ፡ ጥቅም ፡ ሲፈትነኝ
ሁሉ ፡ እያለ ፡ ከእኔ ፡ ጋራ ፡ አፌ ፡ ከንቱ ፡ መቼ ፡ አወራ
ለማመስገን ፡ ለውዳሴ ፡ ይበቃኛል ፡ እስትንፋሴ
አዝ፦ ላመስግነው ፡ ሲጠበቅ ፡ እንባዬ ፡ ላመስግነው
ላመስግነው ፡ ሲጠበቅ ፡ ሀዘኔ ፡ ላመስግነው
ላመስግነው ፡ ሲጠበቅ ፡ ለቅሶዬ ፡ ላመስግነው
ላመስግነው ፡ ሲጠበቅ ፡ ሀዘኔ ፡ ላመስግነው
የሰጠውን ፡ ጌታ ፡ ቢነሳ ፡ ስላለው ፡ ነው ፡ ያን ፡ የሚያስረሳ
ሊያልፍ ፡ ነገር ፡ አላማርርም ፡ ምሥጋናዬን ፡ አላጓድልም
የሰጠውን ፡ ጌታ ፡ ቢወስደው ፡ ስላለው ፡ ነው ፡ ያን ፡ የሚበልጠው
ሊያልፍ ፡ ነገር ፡ አላማርርም ፡ ምሥጋናዬን ፡ አላጓድልም
ላመስግነው ፡ ቢጐድልም ፡ ቢሞላ ፡ ላመስግነው ፡ አምላክ ፡ የለኝ ፡ ሌላ
ላመስግነው ፡ ዛሬ ፡ ያለኝ ፡ ቢነሳ ፡ ላመስግነው ፡ ትላንትን ፡ አልረሳ
ላመስግነው ፡ ቢጐድልም ፡ ቢሞላ ፡ ላመስግነው ፡ አምላክ ፡ የለኝ ፡ ሌላ
ላመስግነው ፡ እምነቴ ፡ ቢለካ ፡ ላመስግነው ፡ ለበጐ ፡ ነው ፡ ለካ
ከባርነት ፡ ሲያሻግረኝ ፡ ጠላቶቼን ፡ ሲጥልልኝ
ከበሮ ፡ ይዤ ፡ እንደዘመርኩ ፡ ተዓምራቱን ፡ እንደተረኩ
ዛሬም ፡ ሳልፍ ፡ በበረሃው ፡ አንደኛ ፡ ነኝ ፡ ለምሥጋናው
እየታየኝ ፡ ከፊት ፡ ተስፋ ፡ ላመስግነው ፡ ከምከፋ

|