እኔ ፡ አላየሁም (Enie Alayehum) - ዳግማዊ ፡ ጥላሁን

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ዳግማዊ ፡ ጥላሁን
(Dagmawi Tilahun)

Dagmawi Tilahun 3.jpg


(3)

ፍቅር ፡ ይቅር ፡ ያለው
(Feqer Yeqer Yalew)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፩ (2009)
ቁጥር (Track):

(10)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የዳግማዊ ፡ ጥላሁን ፡ አልበሞች
(Albums by Dagmawi Tilahun)

ልቤ ፡ ያመነብህ ፡ ውስጤ ፡ ያረፈብህ
የሕይወቴ ፡ ዋልታ ፡ ሁሉን ፡ የጣልኩብህ
ልቤ ፡ ያመነብህ ፡ ውስጤ ፡ ያረፈብህ
የቤቴን ፡ ምሰሶ ፡ ሁሉን ፡ የጣልኩብህ

እኔ ፡ አላየሁም ፡ አንተን ፡ መሳይ
እኔ ፡ አላየሁም ፡ ውስጤን ፡ የሚያይ
እኔ ፡ አላየሁም ፡ ማን ፡ አለኝና
እኔ ፡ አላየሁም ፡ ፍቅሩ ፡ የፀና (፪x)

ልዩ ፡ ነው ፡ ፍቅርህ (፪x)
ልዩ ፡ ነው ፡ መውደድህ (፪x)

ምኔን ፡ አይቶ ፡ ነው ፡ ምን ፡ ተገኝቶብኝ
ከሰዉ ፡ መሃል ፡ ዓይኑ ፡ ያረፈብኝ
ለፍቅር ፡ ብሎ ፡ ያልሆነው ፡ የለም
በባዶ ፡ የሚወድ ፡ እኔ ፡ አላየሁም

እኔ ፡ አላየሁም ፡ አንተን ፡ መሳይ
እኔ ፡ አላየሁም ፡ ውስጤን ፡ የሚያይ
እኔ ፡ አላየሁም ፡ ማን ፡ አለኝና
እኔ ፡ አላየሁም ፡ ፍቅሩ ፡ የፀና (፪x)

ልዩ ፡ ነው ፡ ፍቅርህ (፪x)
ልዩ ፡ ነው ፡ መውደድህ (፪x)

እኔ ፡ አላየሁም ፡ ሞቶ ፡ ሚታደግ
እኔ ፡ አላየሁም ፡ ሕያው ፡ የሚያደር
እኔ ፡ አላየሁም ፡ በነፍሱ ፡ ቤዛ
እኔ ፡ አላየሁም ፡ ሁሉን ፡ የገዛ

እኔ ፡ አላየሁም ፡ ዘሬም ፡ አልሰማ
እኔ ፡ አላየሁም ፡ ኧረ ፡ እንዳንተማ
እኔ ፡ አላየሁም ፡ ለሁሉ ፡ አሳቢ
እኔ ፡ አላየሁም ፡ ፍቅሩ ፡ ሰፊ

ልቤ ፡ ያመነብህ ፡ ውስጤ ፡ ያረፈብህ
የሕይወቴ ፡ ዋልታ ፡ ሁሉን ፡ የጣልኩብህ
ልቤ ፡ ያመነብህ ፡ ውስጤ ፡ ያረፈብህ
የቤቴን ፡ ምሰሶ ፡ ሁሉን ፡ የጣልኩብህ

እኔ ፡ አላየሁም ፡ አንተን ፡ መሳይ
እኔ ፡ አላየሁም ፡ ውስጤን ፡ የሚያይ
እኔ ፡ አላየሁም ፡ ማን ፡ አለኝና
እኔ ፡ አላየሁም ፡ ፍቅሩ ፡ የፀና (፪x)

የዛሬውን ፡ እንጂ ፡ የነገው
ማን ፡ ያውቃል ፡ ምን ፡ እንደሚያረገው
ትላንትን ፡ ሳስበው ፡ አመንኩት
አሳልፌ ፡ በእጁ ፡ ሰጠሁት (፪x)

ልቤን ፡ በፍቅርህ ፡ ነፍሴን ፡ በምክርህ
የምታረካ ፡ አንተ ፡ ብቻ ፡ ነህ
ሚስጥረኛዬ ፡ የልቤ ፡ የምለው
እኔን ፡ የሚያውቀኝ ፡ እንዳንተ ፡ ማነው

እኔ ፡ አላየሁም ፡ አንተን ፡ መሳይ
እኔ ፡ አላየሁም ፡ ውስጤን ፡ የሚያይ
እኔ ፡ አላየሁም ፡ ማን ፡ አለኝና
እኔ ፡ አላየሁም ፡ ፍቅሩ ፡ የፀና (፫x)


ፍቅሩ