በአንተ ፡ ነው (Bante New) - ዳግማዊ ፡ ጥላሁን

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ዳግማዊ ፡ ጥላሁን
(Dagmawi Tilahun)

Dagmawi Tilahun 3.jpg


(3)

ፍቅር ፡ ይቅር ፡ ያለው
(Feqer Yeqer Yalew)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፩ (2009)
ቁጥር (Track):

(6)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የዳግማዊ ፡ ጥላሁን ፡ አልበሞች
(Albums by Dagmawi Tilahun)

ያለፍ ፡ ያለፈው ፡ ኦሆ ፡ ሆ ፡ ኦሆ
ኢየሱስ ፡ በአንተ ፡ ነው ፡ ኦሆ፡ ሆ ፡ ኦሆ (፪x)

አዝ፦ በአንተ ፡ ነው ፡ ነገሬ ፡ ቢያምር
በአንተ ፡ ነው ፡ ቆሜ ፡ ብዘምር
በአንተ ፡ ነው ፡ ካንተ ፡ የተነሳ
በአንተ ፡ ነው ፡ ሥምህ ፡ ይነሳ (፪x)

ሥምህ ፡ ይነሳ ፡ ይነሳ ፡ ሥምህ ፡ ይነሳ
በረሃው ፡ ገነት ፡ ሆነልኝ ፡ ከአንተ ፡ የተነሳ
ሥምህ ፡ ይከበር ፡ ይከበር ፡ ሥምህ ፡ ይከበር
አንተ ፡ ባትረዳኝ ፡ ይሄኔ ፡ የት ፡ እሆን ፡ ነበር

እንዴት ፡ እረሳለሁ ፡ ጠላቶች ፡ ከበውኝ
እንዴት ፡ እረሳለሁ ፡ ከዛ ፡ እንደወጣሁኝ
እንዴት ፡ እረሳለሁ ፡ መሞት ፡ ነበረብኝ
እንዴት ፡ እረሳለሁ ፡ በአንተ ፡ ግን ፡ ተረፍኩኝ (፪x)

አልረሳዉ ፡ (አልረሳም) ፡ ውለታህን ፡ (አልረሳም)
አልረሳዉ ፡ (አልረሳም) ፡ ያረከውን ፡ (አልረሳም)

ያኔ ፡ ሃዘን ፡ በልቤ ፡ ገብቶ ፡ ስታወክ
ያኔ ፡ መፍትሔ ፡ አጥቼ ፡ ውስጤ ፡ ሲጨነቅ
ያኔ ፡ ሰው ፡ አይረዳኝ ፡ የልቤን ፡ አያይ
ያኔ ፡ በአንተኮ ፡ ባይሆን ፡ ዛሬንም ፡ አላይ

ሥምህ ፡ ይነሳ ፡ ይነሳ ፡ ሥምህ ፡ ይነሳ
በረሃው ፡ ገነት ፡ ሆነልኝ ፡ ከአንተ ፡ የተነሳ
ሥምህ ፡ ይከበር ፡ ይከበር ፡ ሥምህ ፡ ይከበር
አንተ ፡ ባትረዳኝ ፡ ይሄኔ ፡ የት ፡ እሆን ፡ ነበር

ያለፍ ፡ ያለፈው ፡ ኦሆ ፡ ሆ ፡ ኦሆ
ኢየሱስ ፡ በአንተ ፡ ነው ፡ ኦሆ ፡ ሆ ፡ ኦሆ (፪x)

አዝ፦ በአንተ ፡ ነው ፡ ነገሬ ፡ ቢያምር
በአንተ ፡ ነው ፡ ቆሜ ፡ ብዘምር
በአንተ ፡ ነው ፡ ከአንተ ፡ የተነሳ
በአንተ ፡ ነው ፡ ሥምህ ፡ ይነሳ (፪x)

ሥምህ ፡ ይነሳ ፡ ይነሳ ፡ ሥምህ ፡ ይነሳ
በረሃው ፡ ገነት ፡ ሆነልኝ ፡ ከአንተ ፡ የተነሳ
ሥምህ ፡ ይከበር ፡ ይከበር ፡ ሥምህ ፡ ይከበር
አንተ ፡ ባትረዳኝ ፡ ይሄኔ ፡ የት ፡ እሆን ፡ ነበር

እንዴት ፡ እረሳለሁ ፡ ከአዕምሮ ፡ በላይ ፡ ነው
እንዴት ፡ እረሳለሁ ፡ ለእኔ ፡ ያደረከው
እንዴት ፡ እረሳለሁ ፡ አክትሞ ፡ እያየሁት
እንዴት ፡ እረሳለሁ ፡ በአንተ ፡ ያገኘሁት (፪x)

አልረሳውም ፡ (አልረሳም) ፡ ውለታህን ፡ (አልረሳም)
አልረሳውም ፡ (አልረሳም) ፡ ያረከውን ፡ (አልረሳም) (፪x)