አይረሳም (Ayresam) - ዳግማዊ ፡ ጥላሁን

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ዳግማዊ ፡ ጥላሁን
(Dagmawi Tilahun)

Dagmawi Tilahun 3.jpg


(3)

ፍቅር ፡ ይቅር ፡ ያለው
(Feqer Yeqer Yalew)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፩ (2009)
ቁጥር (Track):

፲ ፫ (13)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የዳግማዊ ፡ ጥላሁን ፡ አልበሞች
(Albums by Dagmawi Tilahun)

መልካም ፡ ዘመን ፡ ወይም ፡ ክፉ
አያወጡኝ ፡ ከእቅፉ
ዓይን ፡ ያላየው ፡ ጆሮ ፡ ያልሰማው
አለው ፡ ለእኔ ፡ ያዘጋጀው

አጋጣሚውን ፡ ልቤ ፡ አይቶ
አይሸፍትም ፡ ከሱ ፡ ወጥቶ
ግራ ፡ ገብቶኝ ፡ ዝዬ ፡ አልቅሼ
ጌታ ፡ አይደል ፡ ዎይ ፡ አስታዋሼ

አዝ፦ አይረሳም ፡ ሰው ፡ አይረሳም (፬x)

እስኪ ፡ ልናገር ፡ ካልኩት ፡ በላይ ፡ ነው ፡ የእርሱ ፡ ነገር
በዓለም ፡ ያልታየ ፡ በሰው ፡ የሌለ ፡ የሰማይ ፡ ፍቅር
እስኪ ፡ ልናገር ፡ ካልኩት ፡ በላይ ፡ ነው ፡ የእርሱ ፡ ስራ
በዓለም ፡ ያልታየ ፡ በሰው ፡ የሌለ ፡ አያልቅ ፡ ቢወራ

እጄን ፡ ይዞ ፡ እንዳልዎድቅ
ሲራራልኝ ፡ ሲጠነቅቅ
አቤት ፡ ሲያዝን ፡ አቤት ፡ ሲሳሳ
የኔን ፡ ነገር ፡ ፍፁም ፡ አይረሳ (፪x)

አዝ፦ አይረሳም ፡ ሰው ፡ አይረሳም (፬x)

ስላለፈው ፡ ስጨነቅ
ስለነገው ፡ ስታወክ
መለስ ፡ ስል ፡ ወደ ፡ ልቤ
ጌታ ፡ እኮ ፡ አለ ፡ አጠገቤ

ምክንያቱ ፡ ነው ፡ ለመኖሬ
ለሱኮ ፡ ነው ፡ መፈጠሬ
ከበደኝ ፡ አይል ፡ ሲሸከመኝ
ከኔ ፡ ጋር ፡ ነው ፡ መቼ ፡ ረሳኝ

እስኪ ፡ ልናገር ፡ ካልኩት ፡ በላይ ፡ ነው ፡ የእርሱ ፡ ነገር
በዓለም ፡ ያልታየ ፡ በሰው ፡ የሌለ ፡ የሰማይ ፡ ፍቅር
እስኪ ፡ ልናገር ፡ ካልኩት ፡ በላይ ፡ ነው ፡ የእርሱ ፡ ስራ
በዓለም ፡ ያልታየ ፡ በሰው ፡ የሌለ ፡ አያልቅ ፡ ቢወራ

እጄን ፡ ይዞ ፡ እንዳልዎድቅ
ሲራራልኝ ፡ ሲጠነቅቅ
አቤት ፡ ሲያዝን ፡ አቤት ፡ ሲሳሳ
የእኔን ፡ ነገር ፡ ፍፁም ፡ አይረሳ (፪x)

አዝ፦ አይረሳም ፡ ሰው ፡ አይረሳም (፬x)

እናት ፡ ልጇን ፡ ብትረሳ
ዓይኗን ፡ ከእርሱ ፡ ብታነሳ
ብትሸከም ፡ አልፈጠረች
እንደሌላው ፡ ሰው ፡ እኮ ፡ ነች

በእስትንፋሱ ፡ የሰራኝ ፡ ግን
ሊያጣኝ ፡ አይወድ ፡ ሌትና ፡ ቀን
ዋጋ ፡ ከፍሎ ፡ ዋጋ ፡ ሰጠኝ
መች ፡ ሊረሳ ፡ መች ፡ ሊተወኝ

ለካ ፡ ሸክሙ ፡ የሚከብደው
ሰው ፡ ለብቻው ፡ ሲዪዘው ፡ ነው
ሲደርስልኝ ፡ በድካሜ
እርፍ ፡ አልኩኝ ፡ ከህመሜ

ቀን ፡ ያነሳው ፡ ቀን ፡ ቢሽረው
ጌታ ፡ ያሰበውን ፡ ሰው ፡ አይጥለው
በንስር ፡ ክንፍ ፡ በከፍታ
ያወጣኛል ፡ የእኔ ፡ ጌታ

አዝ፦ አይረሳም ፡ ሰው ፡ አይረሳም (፬x)