From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
ያረገልኝ ፡ እንዴት ፡ ይረሳል
አበቃ ፡ ስል ፡ ጌታ ፡ ጀምሯል (፪x)
ውለታው ፡ ብዙ ፡ ብዙ
ፍቅሩ ፡ ብዙ ፡ ብዙ
ሰላሙ ፡ ብዙ ፡ ብዙ
ምህረቱ ፡ ብዙ ፡ ብዙ
ጌታ ፡ አለብኝ ፡ ያንተ ፡ ውለታ (፬x)
መች ፡ እዘገናለሁ ፡ የትላንቱን
አስታውሰዋለሁ ፡ እያንዳንዱን (፪x)
እኔ ፡ ነኝ ፡ የማውቀው ፡ እኔ ፡ ነኛ
ከጐኔ ፡ ሰው ፡ ሳይኖር ፡ ወይ ፡ ጓደኛ
እኔ ፡ ነኝ ፡ የማውቀው ፡ እኔ ፡ ነኛ
የዛሬው ፡ ከፍታ ፡ ታየልኛ (፪x)
አዝ፦ አየልኛ ፡ ብዙ ፡ መልካም
አየልኛ ፡ ለኔው ፡ ሰላም
አየልኛ ፡ ብዙ ፡ እረፍት
አየልኛ ፡ የማልፍበት (፪x)
ያረገልኝ ፡ እንዴት ፡ ይረሳል
አበቃ ፡ ስል ፡ ጌታ ፡ ጀምሯል (፪x)
ውለታው ፡ ብዙ ፡ ብዙ
ፍቅሩ ፡ ብዙ ፡ ብዙ
ሰላሙ ፡ ብዙ ፡ ብዙ
ምህረቱ ፡ ብዙ ፡ ብዙ
ጌታ ፡ አለብኝ ፡ ያንተ ፡ ውለታ (፬x)
ያ ፡ ታሪኬ ፡ ዛሬ ፡ ተቀይሮ
ሰው ፡ አይቶም ፡ አያውቀኝ ፡ አብሮኝ ፡ ኖሮ
ያ ፡ ታሪኬ ፡ ዛሬ ፡ ተቀይሮ
የቅርብ ፡ አይለየኝ ፡ አብሮኝ ፡ ኖሮ
አትፈልጉ ፡ ሌላ ፡ እኔ ፡ ነኝ
በምህረቱ ፡ ብቻ ፡ የቆምኩኝ
አትፈልጉ ፡ ሌላ ፡ ራሴ ፡ ነኛ
እንዲሁ ፡ በፀጋው ፡ ወደደኛ (፪x)
ወደደኛ ፡ ያኔ ፡ ድሮ
ወደደኛ ፡ ሌላው ፡ ዞሮ
ወደደኛ ፡ ሳይቀየር
ወደደኛ ፡ በዛው ፡ ፍቅር (፪x)
ያረገልኝ ፡ እንዴት ፡ ይረሳል
አበቃ ፡ ስል ፡ ጌታ ፡ ጀምሯል (፪x)
ውለታው ፡ ብዙ ፡ ብዙ
ፍቅሩ ፡ ብዙ ፡ ብዙ
ሰላሙ ፡ ብዙ ፡ ብዙ
ምህረቱ ፡ ብዙ ፡ ብዙ
ጌታ ፡ አለብኝ ፡ ያንተ ፡ ውለታ (፬x)
|