አለኝ ፡ ደስ ፡ ደስ (Alegn Des Des) - ዳግማዊ ፡ ጥላሁን

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ዳግማዊ ፡ ጥላሁን
(Dagmawi Tilahun)

Dagmawi Tilahun 3.jpg

(3)

ፍቅር ፡ ይቅር ፡ ያለው
(Feqer Yeqer Yalew)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፩ (2009)
ቁጥር (Track):

(9)

ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የዳግማዊ ፡ ጥላሁን ፡ አልበሞች
(Albums by Dagmawi Tilahun)

አምላክ ፡ እንደሌለው ፡ እንደማንም ፡ ሰዉ
አይወጣኝም ፡ ክፉ ፡ ቃልህ ፡ ጊዜ ፡ አለዉ
እንደመልህቅ ፡ ይዞ ፡ አይለቀኝም ፡ ፍቅርህ
ስጐዳብህ ፡ አይቶ ፡ ለካ ፡ አይችልም ፡ ልብህ (፪x)

ጌታዬ ፡ በግርማ ፡ ሞገስ ፡ ጌታዬ ፡ ቤቴ ፡ ስትደርስ
ጌታዬ ፡ ነፍሴን ፡ መለስካት ፡ ጌታዬ ፡ አለኝ ፡ ደስ ፡ ደስ (፪x)

አዝ፦ አለኝ ፡ ደስ ፡ ደስ ፡ እኔማ ፡ ልመና ፡ የእኔ ፡ ሲሰማ (፪x)

እንደሰው ፡ አይደለም ፡ ነገር ፡ አሰራሩ
ከእለታት ፡ አንድ ፡ ቀን ፡ አያበቃም ፡ ፍቅሩ
መከራ ፡ እንደፈሳሽ ፡ ሲያልፍብኝ ፡ በላዬ
ዘንበል ፡ አለ ፡ ፊትህ ፡ አየኸኝ ፡ ጌታዬ (፪x)

ጌታዬ ፡ በግርማ ፡ ሞገስ ፡ ጌታዬ ፡ ቤቴ ፡ ስትደርስ
ጌታዬ ፡ ነፍሴን ፡ መለስካት ፡ ጌታዬ ፡ አለኝ ፡ ደስ ፡ ደስ (፪x)

የአማልክት ፡ የጭፍሮች ፡ አምላክ ፡ ልመናዬን ፡ ሰምተኸው ፡ ደረስክ
መኳንንቱ ፡ በሩን ፡ ክፈቱ ፡ ውዴ ፡ ይግባ ፡ ደርሷል ፡ ሰዓቱ
ያ ፡ መንፈሱ ፡ የመድሃኒቴ ፡ ይሰማኛል ፡ ገብቶ ፡ ከቤቴ

አዝ፦ አለኝ ፡ ደስ ፡ ደስ ፡ እኔማ ፡ ልመና ፡ የእኔ ፡ ሲሰማ (፪x)

አምላክ ፡ እንደሌለው ፡ እንደማንም ፡ ሰዉ
አይወጣኝም ፡ ክፉ ፡ ቃልህ ፡ ጊዜ ፡ አለዉ
እንደመልህቅ ፡ ይዞ ፡ አይለቀኝም ፡ ፍቅርህ
ስጐዳብህ ፡ አይቶ ፡ ለካ ፡ አይችልም ፡ ልብህ (፪x)

ጌታዬ ፡ በግርማ ፡ ሞገስ ፡ ጌታዬ ፡ ቤቴ ፡ ስትደርስ
ጌታዬ ፡ ነፍሴን ፡ መለስካት ፡ ጌታዬ ፡ አለኝ ፡ ደስ ፡ ደስ (፪x)

አዝ፦ አለኝ ፡ ደስ ፡ ደስ ፡ እኔማ ፡ ልመና ፡ የእኔ ፡ ሲሰማ (፪x)

የአማልክት ፡ የጭፍሮች ፡ አምላክ ፡ ልመናዬን ፡ ሰምተኸው ፡ ደረስክ
መኳንንቱ ፡ በሩን ፡ ክፈቱ ፡ ውዴ ፡ ይግባ ፡ ደርሷል ፡ ሰዓቱ
ያ ፡ መንፈሱ ፡ የመድሃኒቴ ፡ ይሰማኛል ፡ ገብቶ ፡ ከቤቴ

አዝ፦ አለኝ ፡ ደስ ፡ ደስ ፡ እኔማ ፡ ልመና ፡ የእኔ ፡ ሲሰማ (፪x)

ተመስላሎ ፡ መኖር ፡ እያለ ፡ የሚቀለው
ሞኝ ፡ ነው ፡ ቢሉኝም ፡ ሰዎች ፡ ሳይገባቸው
ቢገድለኝም ፡ እንኳን ፡ ልጠብቀው ፡ እሱን
ሲፈልጓት ፡ ሲሿት ፡ ያዳነልኝ ፡ ነፍሴን ፡ የመለሳት ፡ ነፍሴን

አዝ፦ አለኝ ፡ ደስ ፡ ደስ ፡ እኔማ ፡ ልመና ፡ የኔ ፡ ሲሰማ (፪x)