አቻ ፡ አልተገኘልህም (Acha Altegegnelehem) - ዳግማዊ ፡ ጥላሁን

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ዳግማዊ ፡ ጥላሁን
(Dagmawi Tilahun)

Dagmawi Tilahun 3.jpg


(3)

ፍቅር ፡ ይቅር ፡ ያለው
(Feqer Yeqer Yalew)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፩ (2009)
ቁጥር (Track):

(3)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የዳግማዊ ፡ ጥላሁን ፡ አልበሞች
(Albums by Dagmawi Tilahun)

ሁሉም ፡ ያበጀውን ፡ አምላኩን ፡ ሲጠራ
የአማልክቱን ፡ ሥም ፡ በተራ ፡ በተራ
አንድ ፡ ጊዜ ፡ ብቻ ፡ አቤቱ ፡ ስለዉ
እሳት ፡ ሆኖ ፡ መጣ ፡ አቻ ፡ የሌለዉ

አቻ ፡ አቻ ፡ የሌለው (፬x)

አላየንም ፡ ሌላ ፡ አላየንም
ሚሾም ፡ ሚሽር ፡ የለው ፡ ሥልጣኑን
አላየንም ፡ ሌላ ፡ አላየንም
አጋዥ ፡ አጋር ፡ የለው ፡ መንግስቱን (፪x)

አቻ ፡ አቻ ፡ የሌለው (፬x)

(አሃ ፡ አሃሃ) ፡ ሁሌ ፡ እርሱ ፡ ሌላ ፡ አይሻ
(አሃ ፡ አሃሃ) ፡ አልፋ ፡ ነው ፡ መጨረሻ
(አሃ ፡ አሃሃ) ፡ የዕውቀት ፡ ራስ ፡ የጽድቅ ፡ ጫፍ
(አሃ ፡ አሃሃ) ፡ ይኖራል ፡ ስንቱ ፡ ሲያልፍ

(አሃ ፡ አሃሃ) ፡ በዕድሜው ፡ አንድ ፡ ቀን
(አሃ ፡ አሃሃ) ፡ ሲሸነፍ ፡ አላየንም
(አሃ ፡ አሃሃ) ፡ ፎክረው ፡ ሲጨርሱ
(አሃ ፡ አሃሃ) ፡ ያኔ ፡ ነው ፡ እርሱ ፡ መልሱ

አቻ ፡ አልተገኘልህም ፡ ወደር ፡ አልተገኘልህም (፬x)

ቀዳማዊ ፡ እርሱ ፡ ነው ፡ የሁሉም ፡ ፊተኛ
ግርማዊም ፡ እርሱ ፡ ነው ፡ ስልጣኑ ፡ ብቸኛ
በቤተ-መንግስቱ ፡ በዙፋኑ ፡ ላይ
ሌላው ፡ ዝቅ ፡ ብሎ ፡ እርሱ ፡ ከብሮ ፡ ይታይ

ይታይ ፡ እርሱ ፡ ከብር ፡ ይታይ (፬x)

አላየንም ፡ ሌላ ፡ አለየንም ፡ (አላየንም)
ሚሾም ፡ ሚሽር ፡ የለው ፡ ስልጣኑን ፡ (ሥልጣኑን)
አላየንም ፡ ሌላ ፡ አለየንም ፡ (አላየንም)
አጋዥ ፡ አጋር ፡ የለው ፡ መንግስቱን ፡ (መንግስቱን)

አቻ ፡ አቻ ፡ የሌለው (፰x)