የአምላኬ ፡ ቃል ፡ አያረጅም (Yeamlakie Qal Ayarejem) - ሃና ፡ ተክሌ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ሃና ፡ ተክሌ
(Hanna Tekle)

Yeqaleh Fechi Yaberal.jpg

የቃልህ ፡ ፍቺ ፡ ያበራል
(Yeqaleh Fechi Yaberal)
ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፮ (2013)
ቁጥር (Track):

(2)

ርዝመት (Len.): 5:37
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
ሌሎች ፡ የቡድን ፡ አልበሞች
(Other Collection Albums

በማይሆን ፡ መንገድ ፡ ስራመድ
አልፌም ፡ ስንገዳገድ
ቃልህ ፡ ነው ፡ መካሪዬ
ቃልህ ፡ ነው ፡ መላሼ
አልፎ ፡ ስንት ፡ ዘመን
ገስግሶ ፡ ስንት ፡ ዓመት
አልተለወጠም ፡ ሕያው ፡ ነው
አይለወጥም ፡ ፅኑ ፡ ነው

የቃልህ ፡ ፍቺ ፡ ያበራል
አልተለወጠም ፡ ዛሬም ፡ ይሰራል
ዘለዓለም ፡ ይኖራል ፡ እያበራ
ከሚያምኑት ፡ ጋራ

አዝ፦ የአምላኬ ፡ ቃል ፡ አያረጅም
የኢየሱስ ፡ ቃል ፡ አያረጅም
ዘለዓለም ፡ ይኖራል ፡ እያበራ
ከሚያምኑት ፡ ጋራ (፪x)

ከዘመን ፡ በፊት ፡ ብዙ ፡ ኖሯል
ዛሬም ፡ ዘመኑን ፡ ይቀድማል
ለነፍስ ፡ ይዘምራል ፡ ለነፍስ ፡ ይናገራል
ለእስረኛው ፡ መፈታት ፡ ነው
ለጨለማው ፡ ንጋት
መፍትሄ ፡ አለው ፡ ለሁሉም
መልስ ፡ ነው ፡ ለሚሰሙ

በአዋቂዎች ፡ ዕውቀት ፡ ብዛት
አያውቀውም ፡ እርሱ ፡ መረታት
ዘለዓለም ፡ ይኖራል ፡ እያበራ
ከሚያምኑት ፡ ጋራ

አዝ፦ የአምላኬ ፡ ቃል ፡ አያረጅም
የኢየሱስ ፡ ቃል ፡ አያረጅም
ዘለዓለም ፡ ይኖራል ፡ እያበራ
ከሚያምኑት ፡ ጋራ (፪x)

ሆሆሆሆ ፡ ሆሆሆሆ
የቃልህ ፡ ጉልበቱ ፡ የቃልህ ፡ ውበቱ
በዘመን ፡ መካከል ፡ ይገርማል ፡ ጽናቱ
ዘለዓለም ፡ ይኖራል ፡ እያበራ
ከሚያምኑት ፡ ጋራ
ሰርክ ፡ አዲስ ፡ ነው ፡ ከቶ ፡ አይሰለችም
ቢደገም ፡ ቢደገም ፡ ከቶ ፡ አይጠገብም
ዘለዓለም ፡ ይኖራል ፡ እያበራ
ከሚያምኑት ፡ ጋራ
በአዋቂዎች ፡ ዕውቀት ፡ በሊቃውንት ፡ ብዛት
ይረታል ፡ እንጂ ፡ አያውቅም ፡ መረታት
ዘለዓለም ፡ ይኖራል (፫x)
ዘለዓለም ፡ ይኖራል ፡ እያበራ ፡ ከሚያምኑት ፡ ጋራ

ዘለዓለም ፡ ዘለዓለም ፡ ዘለዓለም
ዘለዓለም ፡ ይኖራል
ዘለዓለም ፡ ዘለዓለም ፡ ዘለዓለም ፡ ዘለዓለም ፡ ይኖራል
ዘለዓለም ፡ ይኖራል

በማይሆን ፡ መንገድ ፡ ስራመድ
አልፌም ፡ ስንገዳገድ
ቃልህ ፡ ነው ፡ መካሪዬ
ቃልህ ፡ ነው ፡ መላሼ
አልፎ ፡ ስንት ፡ ዘመን
ገስግሶ ፡ ስንት ፡ ዓመት
አልተለወጠም ፡ ሕያው ፡ ነው
አይለወጥም ፡ ጽኑ ፡ ነው

የቃልህ ፡ ፍቺ ፡ ያበራል
አልተለወጠም ፡ ዛሬም ፡ ይሰራል
ዘለዓለም ፡ ይኖራል ፡ እያበራ
ከሚያምኑት ፡ ጋራ

አዝ፦ የአምላኬ ፡ ቃል ፡ አያረጅም
የኢየሱስ ፡ ቃል ፡ አያረጅም
ዘለዓለም ፡ ይኖራል ፡ እያበራ
ከሚያምኑት ፡ ጋራ (፪x)
blog comments powered by Disqus