ተነስ (Tenes) - አይዳ ፡ አብረሃም

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
አይዳ ፡ አብረሃም
(Ayda Abraham)

Yeqaleh Fechi Yaberal.jpg

የቃልህ ፡ ፍቺ ፡ ያበራል
(Yeqaleh Fechi Yaberal)
ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፮ (2013)
ቁጥር (Track):

(5)

ርዝመት (Len.): 5:17
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
ሌሎች ፡ የቡድን ፡ አልበሞች
(Other Collection Albums

ዓይኖችህ ፡ ተገልጠው ፡ ብታይ
ማን ፡ እንዳለ ፡ ከአንተ ፡ ጋር
ይገባህ ፡ ነበረ ፡ የተገዛህበት ፡ ዋጋ
በውስጥህ ፡ ያለው ፡ ኢየሱስ ፡ ሕያው ፡ ነው
የተናገረውን ፡ ሊያደርግ ፡ በቃሉ ፡ የታመነ ፡ ነው

አዝ፦ አታውቅም ፡ ወይ ፡ የፈጠረህን
አታውቅም ፡ ወይ ፡ ሁሌ ፡ እንደሚያይህ
አታውቅም ፡ ወይ ፡ እንደሚሰማህ
አታውቅም ፡ ወይ ፡ ለአንተ ፡ እንደሚራራ (፪x)

ጥያቄ ፡ በበዛበት ፡ ዓለም ፡ ብትኖር
ምታየው ፡ ምትሰማው ፡ ሚያታልል ፡ ቢመስል
ኢየሱስ ፡ ከኃጢአት ፡ መቀር ፡ ተፈትኖ ፡ አልፏል
ልብህን ፡ ስጠው ፡ ሊረዳህ ፡ ተዘጋጅቷል

አዝ፦ አታውቅም ፡ ወይ ፡ የፈጠረህን
አታውቅም ፡ ወይ ፡ ሁሌ ፡ እንደሚያይህ
አታውቅም ፡ ወይ ፡ እንደሚሰማህ
አታውቅም ፡ ወይ ፡ ለአንተ ፡ እንደሚራራ (፪x)

አንተ ፡ ታናሽ ፡ መንገድ
ፍጻሜህ ፡ ያማረ ፡ ነው
የመረጠህ ፡ ኢየሱስ ፡ በቃሉ ፡ የታመነ ፡ ነው
ጠቢብም ፡ ሚያደርግህን ፡ ቃል ፡ ብላና
ጐዳናህንም ፡ ደግሞ ፡ በእርሱ ፡ አንጻና
ወንጌሉን ፡ ይዘህ ፡ ተከተለው
ከግብ ፡ ሊያደርስህ ፡ የታመነ ፡ ነው

ተነስ (፪x)
ወንድሜ ፡ ሆይ ፡ ተነስ ፡ ተነስ (፪x)
ተነስ ፡ ተንተ ፡ ሂድ
ተነስ ፡ ወንድሜ ፡ ሆይ
ተነስ ፡ ሆሆሆሆ ፡ ተነስ
ሆሆሆሆ ፡ ህምምምም
blog comments powered by Disqus