ተመሥገን ፡ የምለው (Temesgen Yemelew) - ዳንኤል ፡ አምደሚካኤል

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ዳንኤል ፡ አምደሚካኤል
(Daniel Amdemichael)

Yeqaleh Fechi Yaberal.jpg

የቃልህ ፡ ፍቺ ፡ ያበራል
(Yeqaleh Fechi Yaberal)
ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፮ (2013)
ቁጥር (Track):

(10)

ርዝመት (Len.): 5:50
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
ሌሎች ፡ የቡድን ፡ አልበሞች
(Other Collection Albums

አዝ፦ ሁሌ ፡ ሲነጋ ፡ ሲመሽም ፡ ተመስገን ፡ የምለው
ለምን ፡ እንደሆን ፡ ቢጠየቅ ፡ ምክንያቴ ፡ ብዙ ፡ ነው
ብቻ ፡ እኔ ፡ እስካለሁኝ ፡ ድረስ ፡ ወይ ፡ እርሱ ፡ እስኪመጣ
ክብር ፡ ውዳሴ ፡ ምሥጋኔ ፡ ከአፌ ፡ አይታጣ ፡ ሆሆ
ከአፌ ፡ አይታጣ ፤ ከአፌ ፡ አይታጣ ፡ ሆሆ ፤ ከአፌ ፡ አይታጣ (፪x)
ማለዳ ፡ እህህህ ፡ ማለዳ ፡ አሃሃሃ
ዝማሬ ፡ መልካም ፡ ነው ፡ ለጌታ (፪x)

ዝማሬን ፡ በአፌ ፡ አንተ ፡ ጨምረሃል
ነውር ፡ የሌለበት ፡ መሷዕት ፡ ይገባሃል
በእጄ ፡ ንጽህና ፡ በከንፈሬ ፡ ቃል
እንዳመሰግንህ ፡ ፍቃድህ ፡ ሆኗል
በመንፈስህ ፡ ደስታ ፡ በቃልህ ፡ መከር
እሄው ፡ ዝማሬዬ ፡ ክብርህን ፡ ይናገር (፪x)

አዝ፦ ሁሌ ፡ ሲነጋ ፡ ሲመሽም ፡ ተመስገን ፡ የምለው
ለምን ፡ እንደሆን ፡ ቢጠየቅ ፡ ምክንያቴ ፡ ብዙ ፡ ነው
ብቻ ፡ እኔ ፡ እስካለሁኝ ፡ ድረስ ፡ ወይ ፡ እርሱ ፡ እስኪመጣ
ክብር ፡ ውዳሴ ፡ ምሥጋኔ ፡ ከአፌ ፡ አይታጣ ፡ ሆሆ
ከአፌ ፡ አይታጣ ፤ ከአፌ ፡ አይታጣ ፡ ሆሆ ፤ ከአፌ ፡ አይታጣ
ማለዳ ፡ እህህህ ፡ ማለዳ ፡ አሃሃሃ
ዝማሬ ፡ መልካም ፡ ነው ፡ ለጌታ (፪x)

ኪሩቤል ፡ ሱራፌል ፡ አንተን ፡ ያከብራሉ
ለታላቅነትህ ፡ አንተን ፡ ያከብራሉ
ንጹሁን ፡ አምልኮ ፡ ለአንተ ፡ ያቀርባሉ
አንዱ ፡ ለአንዱ ፡ ያወራል ፡ የፊትህን ፡ ግርማ
ይህንን ፡ ሲያደርጉ ፡ አይታክቱምና ፡ አይሰለቹምና

አዝ፦ ሁሌ ፡ ሲነጋ ፡ ሲመሽም ፡ ተመስገን ፡ የምለው
ለምን ፡ እንደሆን ፡ ቢጠየቅ ፡ ምክንያቴ ፡ ብዙ ፡ ነው
ብቻ ፡ እኔ ፡ እስካለሁኝ ፡ ድረስ ፡ ወይ ፡ እርሱ ፡ እስኪመጣ
ክብር ፡ ውዳሴ ፡ ምሥጋኔ ፡ ከአፌ ፡ አይታጣ ፡ ሆሆ
ከአፌ ፡ አይታጣ ፤ ከአፌ ፡ አይታጣ ፡ ሆሆ ፤ ከአፌ ፡ አይታጣ
ማለዳ ፡ እህህህ ፡ ማለዳ ፡ አሃሃሃ
ዝማሬ ፡ መልካም ፡ ነው ፡ ለጌታ (፪x)
blog comments powered by Disqus