ከባሕር ፡ ይዘልቃል (Kebaher Yezelqal) - ተከስተ ፡ ጌትነት

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ተከስተ ፡ ጌትነት
(Tekeste Getnet)

Yeqaleh Fechi Yaberal.jpg

የቃልህ ፡ ፍቺ ፡ ያበራል
(Yeqaleh Fechi Yaberal)
ዓ.ም. (Year): 2013
ቁጥር (Track):

(6)

ርዝመት (Len.): 5:59
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
ሌሎች ፡ የቡድን ፡ አልበሞች
(Other Collection Albums

ጥቂቱን ፡ የሰው ፡ ፍቅር ፡ ዓይኔ ፡ አይቶ ፡ ሲደነቅ
የፍቅር ፡ መጀመሪያው ፡ አንተማ ፡ እንዴት ፡ ትልቅ
ጥቂቱን ፡ የሰው ፡ መውደድ ፡ ዓይኔ ፡ አይቶ ፡ ሲደነቅ
የፍቅር ፡ ጅማሬው ፡ አንተማ ፡ እንዴት ፡ ትልቅ

አዝ፦ ከባሕር ፡ ይዘልቃል ፡ እህህህህህ
የፍቅርህ ፡ ጥልቀቱ ፡ እሆሆሆሆ
ራስህን ፡ አሳንሰህ ፡ ገብተሃል ፡ በየቤቱ
ከባሕር ፡ ይዘልቃል ፡ እህህህህህ
የፍቅርህ ፡ ጥልቀቱ ፡ እሆሆሆሆ
በኢየሱስ ፡ በኩል ፡ መጥተህ ፡ ተገኘህ ፡ በየቤቱ
አቤት ፡ ፍቅር (፬x)
አቤት ፡ መውደድህ (፬x)

ወደድኩህ ፡ ወደድኩሽ ፡ ያለው ፡ ቃላትን ፡ እየቆለለ
ሳይታሰብ ፡ በድንገት ፡ ከስፍራው ፡ ገለል ፡ አለ
በቆላ ፡ ሆነ ፡ በደጋ ፡ በክረምትም ፡ በበጋ
ሕያው ፡ ነው ፡ የአንተስ ፡ ፍቅር ፡ ይለወጥ ፡ ብዬ ፡ አልሰጋ

አዝ፦ ከባሕር ፡ ይዘልቃል ፡ እህህህህህ
የፍቅርህ ፡ ጥልቀቱ ፡ እሆሆሆሆ
ራስህን ፡ አሳንሰህ ፡ ገብተሃል ፡ በየቤቱ
ከባሕር ፡ ይዘልቃል ፡ እህህህህህ
የፍቅርህ ፡ ጥልቀቱ ፡ እሆሆሆሆ
በኢየሱስ ፡ በኩል ፡ መጥተህ ፡ ተገኘህ ፡ በየቤቱ
አቤት ፡ ፍቅር (፬x)
አቤት ፡ መውደድህ (፬x)

አንተ ፡ መልካም ፡ መልክህ
ሁኔታ ፡ የማይለውጥህ
ነገር ፡ የማይለውጥህ
ዘመን ፡ የማይለውጥህ
መልካም ፡ መልካም ፡ መላካም (፪x)
ፍቅርህ ፡ ዘለዓለማዊ ፡ ቸርነትህ ፡ ዘለዓለማዊ
አንተ ፡ ሆይ ፡ አመሰግንሃለሁ
ደግ ፡ ሆይ ፡ አመሰግንሃለሁ
ቸር ፡ ሆይ ፡ እቀኝልሃለሁ
ቸር ፡ ሆይ ፡ እገዛልሃለሁ


ጥቂቱን ፡ ሰው ፡ በጐነት ፡ ዓይኔ ፡ አይቶ ፡ ሲቸገር
የበጐነት ፡ መጀመሪያው ፡ አንተማ ፡ እንዴት ፡ ትልቅ
ጥቂቱን ፡ የሰው ፡ ቸርነት ፡ ዓይኔ ፡ አይቶ ፡ ሲደነቅ
የቸርነት ፡ መደምደሚያው ፡ አንተማ ፡ እንዴት ፡ ትልቅ

አዝ፦ ከባሕር ፡ ይዘልቃል ፡ እህህህህህ
የፍቅርህ ፡ ጥልቀቱ ፡ እሆሆሆሆ
ራስህን ፡ አሳንሰህ ፡ ገብተሃል ፡ በየቤቱ
አቤት ፡ ምህረትህ (፬x)
አቤት ፡ ተዕግስትህ (፬x)
blog comments powered by Disqus