From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
እንዳለፈ ፡ ውኃ ፡ መከራዬን ፡ አስረሳኝ (፪x)
እንደ ፡ ጠዋት ፡ ፀሐይ ፡ ሕይወቴን ፡ አበራው (፪x)
እንደ ፡ ቀትር ፡ ደግሞ ፡ አደመቀው ፡ እንደገና (፪x)
ኧረ ፡ እንደው (፪x) ፡ ምን ፡ ይሻለኛል
ዝም ፡ ብሎ ፡ እግዚአብሔር ፡ ይባርከኛል ፣ ይባርከኛል (፪x)
ኧረ ፡ በረከቱ ፡ ገደብ ፡ አጣ (፬x)
አዎ ፡ ለማዕበሉ ፡ ገደብ ፡ አለው
ለወጀቡ ፡ ገደብ ፡ አለው
ለመከራው ፡ ገደብ ፡ አለው
ግን ፡ ለበረከቱ ፡ ገደብ ፡ የለው (፬x)
እኔ ፡ ዝም ፡ ብዬ ፡ ሳመልክህ
እኔ ፡ ዝም ፡ ብዬ ፡ ሳከብርህ
እኔ ፡ ዝም ፡ ብዬ ፡ ስወድህ
እኔ ፡ ዝም ፡ ብዬ ፡ ስሰጥህ
የሰማያትንም ፡ መስኮቶች ፡ ከፈትክና (፫x)
በረከትን ፡ አወረድከው ፡ እንደገና (፫x)
እንደገና (፬x)
ኧረ ፡ በረከቱ ፡ ገደብ ፡ አጣ (፬x)
እንዴት ፡ ብዬ ፡ ላሳያችሁ
ድንቅ ፡ እኮ ፡ ነው ፡ አምላካችሁ (፫x)
እርሱ ፡ እኮ ፡ ነው ፡ የሞላው
በመስፈሪያው ፡ ሰፈረው
ነቀነቀውና ፡ ጨቆነው (፬x)
ይባርካል ፡ እጁ ፡ ያጠግባል
የልብንም ፡ መሻት ፡ ሁሉ ፡ ይሰጣል
የላይኛውን ፡ እና ፡ የታችኛውን ፡ ምንጪ
ሌላ ፡ ማን ፡ ይሰጣል ፡ እግዚአብሔር ፡ ነው ፡ እንጂ (፪x)
አዎ ፡ ለሀዘኑ ፡ ገደብ ፡ አለው
ለለቅሶውም ፡ ገደብ ፡ አለው
ለጭንቀቱም ፡ ገደብ ፡ አለው
ለእንቆቅልሽ ፡ ገደብ ፡ አለው
ለችግሩ ፡ ገደብ ፡ አለው
ለማጣቱ ፡ ገደብ ፡ አለው
ለበሽታው ፡ ገደብ ፡ አለው
ግን ፡ ለበረከቱ ፡ ገደብ ፡ የለው (፮x)
ኧረ ፡ በረከቱ ፡ ገደብ ፡ አጣ (፮x)
|