From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
አዝ፦ በተቀደሰው ፡ መቅደስህ
ከፍ ፡ ባለው ፡ ዙፋንህ ፡ ላይ
ያለመናወጥ ፡ ጸንተህ ፡ የምትኖር
አንተ ፡ ብቻ ፡ እኮ ፡ ነህ ፡ አምላኬ ፡ ሆይ
በተቀደሰው ፡ መቅደስህ
ከፍ ፡ ባለው ፡ ዙፋንህ ፡ ላይ
ያለመናወጥ ፡ ጸንተህ ፡ የምትኖር
አንተ ፡ ብቻህን ፡ ነህ ፡ ጌታዬ ፡ ሆይ
የቱ ፡ ገብቶኝ ፡ የቱንስ ፡ አውቄ
እንዳስተዋይ ፡ ራሴን ፡ መነቅነቄ
የአንተን ፡ ክብር ፡ የአንተን ፡ ማንነት
ማን ፡ ተረድቶት ፡ ማን ፡ አስተውሎት
ብሞክርም ፡ በቃልህ ፡ ገልጸህ
ከቶ ፡ አልችልም ፡ እንዲህ ፡ ልልህ
ያለኝ ፡ ቋንቋ ፡ በቃ ፡ ይህ ፡ ነውና
እግዚአብሔር ፡ ልበልህ ፡ ገናና
አዝ፦ በተቀደሰው ፡ መቅደስህ
ከፍ ፡ ባለው ፡ ዙፋንህ ፡ ላይ
ያለመናወጥ ፡ ጸንተህ ፡ የምትኖር
አንተ ፡ ብቻ ፡ እኮ ፡ ነህ ፡ አምላኬ ፡ ሆይ
በተቀደሰው ፡ መቅደስህ
ከፍ ፡ ባለው ፡ ዙፋንህ ፡ ላይ
ያለመናወጥ ፡ ጸንተህ ፡ የምትኖር
አንተ ፡ ብቻህን ፡ ነህ ፡ ጌታዬ ፡ ሆይ
በማይታይ ፡ ብርሃን ፡ የደመቀው
መኖሪያህ ፡ በላይ ፡ በሰማያት ፡ ነው
ለዘለዓለም ፡ በቅዱሱ ፡ ስፍራ
የምትኖር ፡ ደግሞ ፡ እየተፈራህ
በስልጣንህ ፡ ሁሉን ፡ የምትገዛ
ባለግርማ ፡ ሞገስህ ፡ የበዛ
ሁሉህ ፡ ከእግርህ ፡ በታች ፡ ተገዝቶልህ
ያለመናወጥ ፡ አንተ ፡ ትኖራለህ
አዝ፦ በተቀደሰው ፡ መቅደስህ
ከፍ ፡ ባለው ፡ ዙፋንህ ፡ ላይ
ያለመናወጥ ፡ ጸንተህ ፡ የምትኖር
አንተ ፡ ብቻ ፡ እኮ ፡ ነህ ፡ አምላኬ ፡ ሆይ
በተቀደሰው ፡ መቅደስህ
ከፍ ፡ ባለው ፡ ዙፋንህ ፡ ላይ
ያለመናወጥ ፡ ጸንተህ ፡ የምትኖር
አንተ ፡ ብቻህን ፡ ነህ ፡ ጌታዬ ፡ ሆይ
ሁሉም ፡ ነገር ፡ ጊዜ ፡ አለው ፡ ሰዓት
ለመውደቁ ፡ ወይ ፡ ለመነሳት
ከፀሐዯ ፡ በታች ፡ አለው ፡ ሁሉ
በየተራ ፡ ይፈራረቃሉ
ተቀያሪ ፡ ተለዋጭ ፡ የሌለህ
ትናንትናም ፡ ዛሬም ፡ ያው ፡ አንተ ፡ ነህ
አይደፈር ፡ ዙፋን ፡ ወንበርህ
እግዚአብሔር ፡ የዘለዓለም ፡ ነህ
አዝ፦ በተቀደሰው ፡ መቅደስህ
ከፍ ፡ ባለው ፡ ዙፋንህ ፡ ላይ
ያለመናወጥ ፡ ጸንተህ ፡ የምትኖር
አንተ ፡ ብቻ ፡ እኮ ፡ ነህ ፡ አምላኬ ፡ ሆይ
በተቀደሰው ፡ መቅደስህ
ከፍ ፡ ባለው ፡ ዙፋንህ ፡ ላይ
ያለመናወጥ ፡ ጸንተህ ፡ የምትኖር
አንተ ፡ ብቻህን ፡ ነህ ፡ ጌታዬ ፡ ሆይ
|