በልቶና ፡ ጠጥቶ (Beltona Teteto) - ለዓለም ፡ ጥላሁን

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ለዓለም ፡ ጥላሁን
(Lealem Tilahun)

Yeqaleh Fechi Yaberal.jpg

የቃልህ ፡ ፍቺ ፡ ያበራል
(Yeqaleh Fechi Yaberal)
ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፮ (2013)
ቁጥር (Track):

(4)

ርዝመት (Len.): 6:35
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
ሌሎች ፡ የቡድን ፡ አልበሞች
(Other Collection Albums

አንድ ፡ ፊት ፡ አለ ፡ እኔ ፡ የለመድኩት
ማልጄ ፡ ልየው ፡ እንደናፈቅሁት
ቀና ፡ ይሆናል ፡ ይሰምራል ፡ ቀኔ
የወዳጄን ፡ ፊት ፡ ካየሁት ፡ እኔ (፪x)

አዝ፦ በልቶና ፡ ጠጥቶ ፡ መኖር ፡ ሕይወት ፡ እንዳልሆነ ፡ ከገባኝ ፡ ሰንብቶ
እግዚአብሔር ፡ እግዚአብሔር ፡ ሚያሰኝ ፡ አንዳች ፡ ነገር ፡ ውስጤ ፡ ገብቶ
በልቶና ፡ ጠጥቶ ፡ መኖር ፡ ሕይወት ፡ እንዳልሆነ ፡ ከገባኝ ፡ ሰንብቶ
አባቴን ፡ አባቴን ፡ ሚያሰኝ ፡ አንዳች ፡ ነገር ፡ ውስጤ ፡ ገብቶ
ሌላውማ ፡ አያምረኝም ፡ እኔ ፡ የኢየሱስ ፡ ነኝ (፪x)
እኔ ፡ የኢየሱሴ ፡ ነኝ (፬x)

የሕይወት ፡ ብቸኛ ፡ ቁም ፡ ነገር
የሆንከው ፡ ወዳጄ ፡ እግዚአብሔር
የሆንከው ፡ ጌታዬ ፡ እግዚአብሔር
በህልውናህ ፡ ውስጥ ፡ መኖር
መታደል ፡ ነው ፡ ትልቅ ፡ ክብር (፪x)

አዝ፦ በልቶና ፡ ጠጥቶ ፡ መኖር ፡ ሕይወት ፡ እንዳልሆነ ፡ ከገባኝ ፡ ሰንብቶ
አባቴን ፡ አባቴን ፡ ሚያሰኝ ፡ አንዳች ፡ ነገር ፡ ውስጤ ፡ ገብቶ
ሌላውማ ፡ አያምረኝም ፡ እኔ ፡ የኢየሱስ ፡ ነኝ (፪x)
እኔ ፡ የኢየሱሴ ፡ ነኝ (፬x)

የእኔ ፡ ሞገስ ፡ የእኔ ፡ ተስፋ
ነፍሴ ፡ እንደ ፡ አንተ ፡ የወደደችው ፡ ጠፋ
ነፍሴ ፡ እንደ ፡ አንተ ፡ የአፈቀረችው ፡ ጠፋ
አንተን ፡ ባየሁበት ፡ ዓይኔ
አልታይ ፡ አለኝ ፡ ሌላው ፡ እኔ (፪x)

በዚህ ፡ በምድር ፡ ላይ ፡ ማጣት ፡ የማልፈልገው
ሌላ ፡ ነገር ፡ አይደለም ፡ አምላኬ ፡ ሆይ ፡ አንተን ፡ ነው (፪x)

አዝ፦ በልቶና ፡ ጠጥቶ ፡ መኖር ፡ ሕይወት ፡ እንዳልሆነ ፡ ከገባኝ ፡ ሰንብቶ
አባቴን ፡ አባቴን ፡ ሚያሰኝ ፡ አንዳች ፡ ነገር ፡ ውስጤ ፡ ገብቶ
ሌላውማ ፡ አያምረኝም ፡ እኔ ፡ የኢየሱስ ፡ ነኝ (፪x)
እኔ ፡ የኢየሱሴ ፡ ነኝ (፬x)




blog comments powered by Disqus