From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
አፍ ፡ አለው ፡ አምላኬ ፡ እርሱ ፡ ይናገራል
እኔ ፡ ዝም ፡ እላለሁ ፡ በስራው ፡ ይከብራል
እጅ ፡ አለው ፡ አምላኬ ፡ ሁሉን ፡ ሰው ፡ ይረዳል
አምኖ ፡ ለተጠጋው ፡ ደካማን ፡ ይወዳል
አምላኬ ፡ ጆሮ ፡ አለው ፡ ለቅሶዬን ፡ ይሰማል
የእምነት ፡ ጸሎቴን ፡ ሁሉን ፡ ይፈጽማል
ዓይን ፡ አለው ፡ አምላኪ ፡ እሁሉን ፡ ነገር ፡ ያያል
የራሱ ፡ ለሆኑት ፡ ዘወትር ፡ ይታደጋል
ክንዱ ፡ ጠንካራ ፡ ነው ፡ አምላኬ ፡ ሲረዳ
መንጥቆ ፡ ያወጣል ፡ ከመከራ ፡ ጓዳ
አምላኬ ፡ ሲቆጣ ፡ እጁን ፡ ሲዘረጋ
ሁሉን ፡ ይቀበላል ፡ የስራውን ፡ ዋጋ
ቃሉ ፡ እጅግ ፡ ኃያል ፡ ነው ፡ የሰው ፡ ልብ ፡ ያቀልጣል
መራራውን ፡ ጣፋጭ ፡ አርጐ ፡ ይለውጣል
አምላኬ ፡ ሲቆጣ ፡ በጅራፍ ፡ ይቀጣል
የምድረበዳውን ፡ አውሬ ፡ ያናውጣል
ጻድቅ ፡ ነው ፡ አምላኬ ፡ በጽድቅ ፡ ይበይናል
ፍርድን ፡ አያጣምም ፡ ጥም ፡ ፍርድን ፡ ይፈርዳል
ፊት ፡ አይቶ ፡ አያዳላ ፡ ለወገኔ ፡ አይል
ከዚህ ፡ ይልቅ ፡ ለዚያ ፡ ብሎ ፡ ማያታልል
በጽድቅ ፡ ወንበሩ ፡ ላይ ፡ ተቀምጦ ፡ ይፈርዳል
ፍርድ ፡ ለጠመመበት ፡ ምላሹን ፡ ይሰጣል
እንደአምላኬ ፡ ያለ ፡ ትክክል ፡ ማን ፡ አለ
ከምድር ፡ ፈራጆች ፡ የላቀ ፡ የተሻለ
አምላኬ ፡ ድምጽ ፡ አለው ፡ ለልብ ፡ ይናገራል
ሃሳብና ፡ ስራንም ፡ ይመረምራል
ነፍስና ፡ መንፈስን ፡ መዝኖ ፡ ሲጠግን
አምላኬ ፡ ሃኪም ፡ ነው ፡ የሰውን ፡ ልብ ፡ ሲያድን
ሁሉም ፡ በእጁ ፡ ነው ፡ ሁሉም ፡ በፍቃዱ
አምላኬ ፡ ሕያው ፡ ነው ፡ ወደ ፡ ሌላ ፡ አትሂዱ
ይህን ፡ ታላቅ ፡ ጌታ ፡ ላስተዋውቃችሁ
አምላኬ ፡ ኢየሱስ ፡ ነው ፡ ይሁን ፡ አምላካችሁ (፫x)
|