ምልክት ፡ አይተናል (Meleket Aytenal) - የተለያዩ ፡ ዘማሪያን

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
የተለያዩ ፡ ዘማሪያን
(Various Artists)
ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፮ (2014)
ርዝመት (Len.): 9:37
ሌሎች ፡ ነጠላ ፡ መዝሙሮች
(Other Singles)
ሌሎች ፡ የየተለያዩ ፡ ዘማሪያን ፡ አልበሞች
(Other Albums ፡ by Various Artists)

የምሥራቹ ፡ ቃል ፡ በምድር ፡ ተሰማ
በከብቶች ፡ በረት ፡ ውስጥ ፡ ቤተልሔም ፡ ከተማ
ምንም ፡ ጊዜው ፡ ቢርቅ ፡ ቢታይም ፡ እርቆ
ኢየሱስ ፡ ተወለደ ፡ ዘመኑን ፡ ጠብቆ

የጨለማ ፡ ዘመን ፡ የፍዳ ፡ ዓመት
ኃጢአት ፡ ጀርባ ፡ ሰጥቶ ፡ የእግዚአብሔርን ፡ ፊት
አምላክ ፡ ሥጋ ፡ ለብሶ ፡ ወደ ፡ ምድር ፡ መጣ
ለኃጢአተኛ፡ ሁሉ ፡ የጽድቅ ፡ ፀሐይ ፡ ወጣ

ባላይ ፡ እኔ ፡ በዓይኔ ፡ በብረቱ ፡ ያውቃል ፡ ስለ ፡ እውነቱ
እኛም ፡ ልንዘምር ፡ መጥተናል ፡ በቤቱ (፪x)

የጨለማ ፡ ዘመን ፡ የፍዳ ፡ ዓመት
ኃጢአት ፡ ጀርባ ፡ ሰጥቶ ፡ የእግዚአብሔርን ፡ ፊት
አምላክ ፡ ሥጋ ፡ ለብሶ ፡ ወደ ፡ ምድር ፡ መጣ
ለኃጢአተኛ፡ ሁሉ ፡ የጽድቅ ፡ ፀሐይ ፡ ወጣ

ባላይ ፡ እኔ ፡ በዓይኔ ፡ በብረቱ ፡ ያውቃል ፡ ስለ ፡ እውነቱ
እኛም ፡ ልንዘምር ፡ መጥተናል ፡ በቤቱ (፬x)

ብንሆንም ፡ ምስኪን ፡ እረኛ
ምልክት ፡ አይተናል ፡ እኛ
አብሳሪ ፡ ሆንን ፡ ተረኛ
የምሥራች ፡ በሉ ፡ ስሙኛ

ተወለደ ፡ የዓለም ፡ መድኃኒት ፡ ሥሙን ፡ እናክብር ፡ በቀን ፡ በሌሊት
(ተወለደ ፡ የዓለም ፡ መድኃኒት ፡ ሥሙን ፡ እናክብር ፡ በቀን ፡ በሌሊት)
እሰይ ፡ እሰይ ፡ ተወለደልን ፡ ምክንያት ፡ ሆነን ፡ ለመዳናችን
(እሰይ ፡ እሰይ ፡ ተወለደልን ፡ ምክንያት ፡ ሆነን ፡ ለመዳናችን) (፪x)

ብንሆንም ፡ ምስኪን ፡ እረኛ
ምልክት ፡ አይተናል ፡ እኛ
አብሳሪ ፡ ሆንን ፡ ተረኛ
የምስራች ፡ በሉ ፡ ስሙኛ

ተወለደ ፡ የዓለም ፡ መድኃኒት ፡ ሥሙን ፡ እናክብር ፡ በቀን ፡ በሌሊት
(ተወለደ ፡ የዓለም ፡ መድኃኒት ፡ ሥሙን ፡ እናክብር ፡ በቀን ፡ በሌሊት)
እሰይ ፡ እሰይ ፡ ተወለደልን ፡ ምክንያት ፡ ሆነን ፡ ለመዳናችን
(እሰይ ፡ እሰይ ፡ ተወለደልን ፡ ምክንያት ፡ ሆነን ፡ ለመዳናችን) (፪x)

ተወለደ (አሆ) ፤ ተወለደ (አሆ)
የዓለም ፡ ፍቅር (አሆ) ፤ ተወለደ (አሆ)
ተወለደ (አሆ) ፤ ተወለደ (አሆ)
የዓለም ፡ ቤዛ (አሆ) ፤ ተወለደ

ኑና ፡ ኑና ፡ ኑና
ኑና ፡ ኑና ፡ ኑና
ኑና ፡ እናመስግን ፡ ኑና (ኑና ፡ ኑና) (፪x)

ኑና ፡ ኑና ፡ ኑና
ኑና ፡ ኑና ፡ ኑና
ህጻን ፡ ተወልዷልና (ኑና ፡ ኑና) (፪x)

ተወለደ (አሆ) ፤ ተወለደ (አሆ)
የዓለም ፡ ፍቅር (አሆ) ፤ ተወለደ (አሆ)
ተወለደ (አሆ) ፤ ተወለደ (አሆ)
የዓለም ፡ ቤዛ (አሆ) ፤ ተወለደ

ኑና ፡ ኑና ፡ ኑና
ኑና ፡ ኑና ፡ ኑና
ኑና ፡ እናመስግን ፡ ኑና (ኑና ፡ ኑና) (፪x)

ኑና ፡ ኑና ፡ ኑና
ኑና ፡ ኑና ፡ ኑና
ህጻን ፡ ተወልዷልና (ኑና ፡ ኑና) (፪x)

ተወለደ (አሆ) ፤ ተወለደ (አሆ)
የዓለም ፡ ፍቅር (አሆ) ፤ ተወለደ (አሆ)
ተወለደ (አሆ) ፤ ተወለደ (አሆ)
የዓለም ፡ ቤዛ (አሆ) ፤ ተወለደ

ዓመተ ፡ ዓለም ፡ ተቀየረልን ፡ በመድኃኒዓለም
(ዓመተ ፡ ዓለም ፡ ተቀየረልን ፡ በመድኃኒዓለም) (፬x)
(ተወልዷል) እንበል
(ተወልዷል) እንቺም ፡ በይ
(ተወልዷል) አንተም ፡ በል
(ተወልዷል) እንበል (፪x)
(ተወልዷል) ኢየሱስ
(ተወልዷል) በግርግም
(ተወልዷል) ተወልዷል
(ተወልዷል) ጌታ
(ተወልዷል) ኢየሱስ
(ተወልዷል) ሁሉን ፡ ቻይ
(ተወልዷል) አዶናይ
(ተወልዷል) አባት
(ተወልዷል) መሲህ
(ተወልዷል) ኢየሱስ (፪x)

ሆሆ ፡ ተወልደ (፬x)
ሆሆ ፡ ተወልደ (፬x)

ሥጋን ፡ ለበሰና ፡ ወደ ፡ ምድር ፡ ወረደ
ሆሆ ፡ ተወልደ (፪x)
የሚከሰን ፡ ጠላት ፡ በእርሱ ፡ ተወገደ
ሆሆ ፡ ተወልደ (፪x)
ሰውና ፡ እግዚአብሔርን ፡ በፍቅር ፡ አዛመደ
ሆሆ ፡ ተወልደ (፪x)
የማሪያም ፡ ልጅ ፡ ኢየሱስ ፡ ለዓለም ፡ አማለደ
ሆሆ ፡ ተወልደ (፪x)

እሰይ ፡ እሰይ ፡ ተወልደልን ፡ የዓለም ፡ ሲሳይ
የዓለም ፡ ቤዛ ፡ የዓለም ፡ መድኃኒት ፡ ቤተልሔም ፡ ላይ
ሥጋን ፡ ለብሶ ፡ ራሱን ፡ አዋርዶ ፡ የተገለጠው
የእግዚአብሔር ፡ ልጅ ፡ ኢየሱስ ፡ ክርስቶስ ፡ አዳኛችን ፡ ነው

ኢየሱስ (ተወለደ) (፰x)

አምጡ ፡ ለእርሱ ፡ ሚገባ ፡ የክብር ፡ እቃ
ከርቤውን ፡ ዕጣኑም ፡ ሳይቀር ፡ ለእርሱ ፡ ይዘማ
በበረት ፡ ተወልዱ ፡ እኛን ፡ ጌጠኛ ፡ ያደረገን
ልናመልክ ፡ ተጠራርተናል ፡ ፍቅሩን ፡ አስበን

ሆሆ ፡ ተወልደ (፬x)

እሰይ ፡ እሰይ ፡ ተወልደልን ፡ የዓለም ፡ ሲሳይ
የዓለም ፡ ቤዛ ፡ የዓለም ፡ መድኃኒት ፡ ቤተልሔም ፡ ላይ
ሥጋን ፡ ለብሶ ፡ ራሱን ፡ አዋርዶ ፡ የተገለጠው
የእግዚአብሔር ፡ ልጅ ፡ ኢየሱስ ፡ ክርስቶስ ፡ አዳኛችን ፡ ነው

ኢየሱስ (ተወለደ) (፰x)