ሀዘን ፡ ወይም ፡ ደስታ (Hazen Weyem Desta)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

ሀዘን ፡ ወይም ፡ ደስታ ፡ የሚደርሰነ ፡ ማን ፡ ያውቃል
መድኃኒታችን ፡ ከእኛ ፡ ዘንድ ፡ ከሆነ ፡ ይበቃናል
በየዋህ ፡ ድምጽህ ፡ ያርፋል ፡ ነፍሳችን
ሰላምና ፡ ደስታ ፡ በጭንቀት ፡ አለን

ህማማት ፡ ሁሉ ፡ በአንተ ፡ ስናምን ፡ ይበርዳል
ኃይል ፡ በድካም ፡ ረድኤት ፡ በመከራችን ፡ ይሆናል
ጭንቀት ፡ የሞላ ፡ ይህ ፡ ምድራዊ ፡ ሕይወት
ከአንተ ፡ ዘንድ ፡ ይሆነናል ፡ ገነት

ምድር ፡ ሲበራ ፡ ኃጢአት ፡ ስለ ፡ በዛ ፡ ይጨልማል
ከአንተ ፡ ከዳን ፡ ስለዘህ ፡ ፈትህ ፡ ከእኛ ፡ ይሰወራል
ወደ ፡ ምህረትህ ፡ እንማጠናለን
በርህሩህ ፡ ብብትህ ፡ አሳርፈን

ኦ ፡ ቸሩ ፡ ኢየሱስ ፡ በሕይወት ፡ በሞትም ፡ ረጃችን ፡ ሁን
አሳልፈን ፡ ከክፋት ፡ ስንገጥም ፡ ስጠን ፡ ድሉን
ሁን ፡ ከእኛ ፡ ዘንድ ፡ ቀናችን ፡ ሲመሽብን
ብርሃን ፡ ሁንልን ፡ ደስታን ፡ አድለን