ሃሌሉያ (Hallelujah)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

1. እግዚአብሔር ፡ አምላክ ፡ የለህ ፡ እኩያ
ሕዝብህ ፡ ሲጨነቅ ፡ በባዕድ ፡ ምድር
በፈርዖን ፡ ግዞት ፡ እጅግ ፡ ሲያማርር
ጩኸቱን ፡ ሰምተህ ፡ ልትረዳው ፡ ወረድክ
በጸናች ፡ እጅህ ፡ ሕዝብህን ፡ ታደክ

2. ሃያል ፡ አምላክ ፡ ነህ ፡ የማትረታ
በሰልፍ ፡ በስልጣን ፡ የምትበረታ
እግዚአብሔር ፡ ሆይ ፡ ታላቅ ፡ አምላክ ፡ ነህ
ከቶ ፡ አይገኝም ፡ አንተን ፡ የሚመስልህ

3. በሰማይ ፡ በምድር ፡ በባህር ፡ በጥልቅ
የወደድከውን ፡ ሁሉ ፡ አደረክ
ይህን ፡ አይቼ ፡ አከበርኩህ
በእግርህ ፡ ወድቄ ፡ ሃሌሉያ ፡ አልኩኝ