ኢየሩሣሌም ፡ ቅድስቲቱ ፡ ከተማ (Eyerusalem Qedestitu Ketema)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

አዝ፦ ኢየሩሣሌም ፡ ቅድስቲቱ ፡ ከተማ
የጐዳናሽ ፡ ውጥንቅጡ ፡ ቢበዛም ፡ እንኳ
ሳላይሽ ፡ አልቀርም ፡ በአምላክ ፡ ኃይል ፡ ዕርዳታ

የናፈቀኝ ፡ ዜማ ፡ የቅዱስ ፡ ዝማሬ ፡ ዝማሬ
አልቀርም ፡ ሳልዘምር ፡ ከፃድቃን ፡ አብሬ
ከበጉ ፡ ዙፋን ፡ ሥር ፡ ሳልዘምር ፡ በደስታ ፡ በደስታ
አልቀርም ፡ ሳላይሽ ፡ አንቺን ፡ ቅድስት ፡ ቦታ

አዝ፦ ኢየሩሣሌም ፡ ቅድስቲቱ ፡ ከተማ
የጐዳናሽ ፡ ውጥንቅጡ ፡ ቢበዛም ፡ እንኳ
ሳላይሽ ፡ አልቀርም ፡ በአምላክ ፡ ኃይል ፡ ዕርዳታ

ማቋረጫው ፡ መንገድ ፡ ሊጠልፈኝ ፡ ቢነሣ ፡ ቢነሣ
ሳላየው ፡ አልቀርም ፡ የይሁዳን ፡ አንበሣ
ብቻዬን ፡ ብቀርም ፡ መንገደኛው ፡ ሸሽቶ ፡ ሸሽቶ
ሳልዘምር ፡ አልቀርም ፡ ኢየሱሴ ፡ መጥቶ

የመናኝ ፡ ተራራ ፡ መቧጠጥ ፡ ቢያቅተኝ ፡ ቢያቅተኝ
የበረሃው ፡ ጉዞ ፡ ውኃ ፡ ጥም ፡ ቢጐዳኝ
የሚያረካው ፡ ጌታ ፡ ቢመጣ ፡ ከሰማይ ፡ ከሰማይ
ይረዳኛል ፡ በዕርግጥ ፡ ያቺን ፡ ቦታ ፡ እንዳይ

አዝ፦ ኢየሩሣሌም ፡ ቅድስቲቱ ፡ ከተማ
የጐዳናሽ ፡ ውጥንቅጡ ፡ ቢበዛም ፡ እንኳ
ሳላይሽ ፡ አልቀርም ፡ በአምላክ ፡ ኃይል ፡ ዕርዳታ