Classics/Bel Efer Telatie
< Classics
|ርዕስ=በል ፡ እፈር ፡ ጠላቴ
|Title=Bel Efer Telatie
|ቋንቋ=አማርኛ
|Language=Amharic
|Lyrics=
- የመጎብኛዬ ፡ ወራት ፡ ሲመጣ
- ለሚፈሩህ ፡ የጽድቅ ፡ ፀሐይ ፡ ደግሞ ፡ ሲወጣ
- ፀሎቴም ፡ ተሰማ
- ጠላት ፡ እየሰማ
- ዕዳዬ ፡ ተከፈለ
- ከሳሼ ፡ የታለ
- ጉልበቴ ፡ በረታ
- በኢየሱስ ፡ ጌታ
አዝ፦ በል ፡ እፈር ፡ ጠላቴ ፡ እዳዬ ፡ ተከፍሏል
- ከየት ፡ ታምጣ ፡ ከሳሼ ፡ ቀንበሬ ፡ ተሰብሯል
- በነጻነት ፡ ልኖር ፡ ነጻ ፡ አውጥቶኛል
- ዳግም ፡ ላልታሰር ፡ ኤፍታ ፡ ብሎ ፡ ለቆኛል
- ክብር ፡ ለስሙ ፡ ይሁን
- ክብር ፡ ላዳነኝ ፡ ይሁን
- ክብር ፡ ለጌታ ፡ ይሁን
- ክብር ፡ ለኢየሱስ ፡ ይሁን
1. ዝናብም ፡ ባይኖር ፡ ነፋስም ፡ ባላይ
- ድል ፡ አውጃለሁ ፡ ባዶ ፡ ተስፋ ፡ ላይ
- ደረቁ ፡ ምድር ፡ ይለመልማል
- በባዶ ፡ ጉድጓድ ፡ ዉሃ ፡ ይሞላል
- ያለቀው ፡ ነገር ፡ ሞልቶ ፡ ይፈሳል
- የተጠማ ፡ ሁሉ ፡ ጠጥቶ ፡ ይረካል
2. ምንም ፡ ቢበዛ ፡ የኔ ፡ መከራ
- ከቶ ፡ ቢጎድል ፡ የወይራ ፡ ሥራ
- ያዳነኝ ፡ ጌታ ፡ ሀይል ፡ ይሆነኛል
- እንደ ፡ ዋላ ፡ እግሬን ፡ ያበረታኝል
- ጠባቂዬ ፡ የሱስ ፡ አቅም ፡ ይሆነኛል
- በከፍታ ፡ ላይ ፡ ያራምደኛል
3. ያመንኩት ፡ ወዳጅ ፡ ቢከዳ ፡ እንኳን
- ቢፈርስ ፡ ቢበተን ፡ ምድራዊ ፡ ድንኳን
- የታመንኩ ፡ ጌታ ፡ ከኔ ፡ ጋር ፡ ያለው
- ያረጀውን ፡ ነገር ፡ አዲስ ፡ ጀመረው
- ማይከዳ ፡ ወዳጅ ፡ ከጎኔ ፡ ያለው
- የታሪክ ፡ መዝገብ ፡ አገላበጠው
- ያመንኩት ፡ የሱስ ፡ ከኔ ፡ ጋር ፡ ያለው
- የሞትን ፡ አዋጅ ፡ ገለባበጠው
4.ሞቶ ፡ ተቀብሮ ፡ ቢሸት ፡ ነገሬ
- አንድም ፡ ባይሰማ ፡ አስደሳች ፡ ወሬ
- ወድቆ ፡ አይቀርም ፡ በከንቱ ፡ ሞቶ
- ሕይወት ፡ ይዘራል ፡ ጌታዬ ፡ መጥቶ
- ትንሣኤ ፡ አለ ፡ ዛሬም ፡ ካባቴ
- በእግሩ ፡ ቆሟል ፡ እፈር ፡ ጠላቴ
አዝ፦ በል ፡ እፈር ፡ ጠላቴ ፡ ብወድቅ ፡ እነሳለሁ
- ቢጨልምብኝም ፡ ብርሃን ፡ እወጣልሁ
- ወደ ፡ እግዚአብሔር ፡ እመለከታለሁ
- መድኃኒቴን ፡ አምላክ ፡ ተስፋ ፡ አደርጋለሁ
- እሱም ፡ ይሰማኛል ፡ ጽድቅን ፡ ያሳየኛል
- እሱም ፡ ያደምጠኛል ፡ እረፍት ፡ ይሰጠኛል