Caleb Tesfaye/Tensae Ale/Yeselam Mefleqiya

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

ዘማሪ ካሌብ ተስፋዬ ርዕስ የሰላም መፍለቂያ አልበም ትንሳኤ አለ

የሰላም መፍለቂያ ምንጭ ነህ ኢየሱሰ አንተ እውነተኛ ዓለም ለቀጣው ሰው ለተጐዳ መጽናኛ የጠፋን ፈላጊ የኃጢአተኛ ወዳጅ ለበዛው በደሉ ጠበቃ ነህ አማላጅ

ስንቱ እረፍት አጥቶ ኖረ መስሎት ብዙ ሞከረ ለፋ ወጣ ገባ ፈልጐ አላገኘም ምህረትህ ቀደመ ከንቱ ሆኖ አልቀረም

የሰላም መፍለቂያ ምንጭ ነህ ኢየሱሰ አንተ እውነተኛ ዓለም ለቀጣው ሰው ለተጐዳ መጽናኛ የጠፋን ፈላጊ የኃጢአተኛ ወዳጅ ለበዛው በደሉ ጠበቃ ነህ አማላጅ

እምቢ አሻፈረኝ ብሎ ሄደ ቤትህን ጥሎ

በፍቅር አባብለህ መለስከው ያንን ሰው አንተን መሳይ አባት ከየት ነው እሚገኘው

የሰላም መፍለቂያ ምንጭ ነህ ኢየሱሰ አንተ እውነተኛ ዓለም ለቀጣው ሰው ለተጐዳ መጽናኛ የጠፋን ፈላጊ የኃጢአተኛ ወዳጅ ለበዛው በደሉ ጠበቃ ነህ አማላጅ

ነፍሱን ለጠሉት ሁሉ ሲል ሰጠ ተቆጠረ እንደ ቂል የሰው ልጆች ክፋት እንዲህ እየጨመረ ምትክ ሆኖ ባይሞት ምን ይኮን ነበረ?

የሰላም መፍለቂያ ምንጭ ነህ ኢየሱሰ አንተ እውነተኛ ዓለም ለቀጣው ሰው ለተጐዳ መጽናኛ የጠፋን ፈላጊ የኃጢአተኛ ወዳጅ ለበዛው በደሉ ጠበቃ ነህ አማላጅ።