የንጋቱ ፡ ኮከብ (Yenegatu Kokeb) - ካሌብ ፡ ተስፋዬ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ካሌብ ፡ ተስፋዬ
(Caleb Tesfaye)

Caleb Tesfaye 6.jpg


(6)

ትንሳኤ ፡ አለ
(Tensae Ale)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፩ (2009)
ቁጥር (Track):

(3)

ርዝመት (Len.): 5:08
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የካሌብ ፡ ተስፋዬ ፡ አልበሞች
(Albums by Caleb Tesfaye)

(አዝማች)
የንጋቱ፡ኮከብ፡ውበቱ፡ያማረ፣
ከምንም፡ከማንም፡በላይ፡የከበረ፣
እሱ፡ነው፡ጌታዬ፥እኔ፡የማመልከው፡
ምሕረቱን፡አብዝቶ፡ልቤን፡ያሳረፈው።

(ቁ 1)
ብዙ ክብር ያርግ፡ ወደ ማደሪያው፣
ዙፋኑን ይክበበው ስለሚገባው፤
አለ የተባለ አዳኝ ብቸኛ መድኃኒት፣
ኢየሱስ እሱ ነው አሁንም ወደፊት።

የንጋቱ ኮከብ ...

(ቁ 2)
ዳግመኛ ተወለድሁ፡ ክፉ ደጉን ለየሁ ፣
አዲስ ምዕራፍ ከፍቶ አሮጌውን ሻረው
የታረደውን በግ አለቃዬ ኢየሱስ፣
ሾምኩት በሕይወቴ ላይ ሊገዛ እንደ ንጉሥ።

የንጋቱ ከክብ...

(ቁ 3)
እንዲሁ ወደደኝ፡ ከነምናምኔ፣
ትቼ ተከተልኩት፣ ይቺ ዓለም ለምኔ?
ማንም ያልሰጠኝን ሰላምና ደስታ፡
አግኝቻለሁ ከላይ ከሠራዊት ጌታ፡፡

የንጋቱ ኮከብ..