From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
አለልኝ ፡ የምልብህ
ትምክህቴ ፡ የምመካብህ
የድሃ ፡ ቀኜ ፡ ምርኩዝ ፡ ነህ
አለኝታ ፡ ነህ ፡ ታኮራለህ
ማንም ፡ ባይኖረኝ ፡ ዙሪያዬ
ማዶ ፡ ቢሆንም ፡ ጓዳዬ
አለሁልህ ፡ የሚል ፡ ቢጠፋ
ጌታ ፡ እኮ ፡ ነህ ፡ የእኔ ፡ ተስፋ
ሰው ፡ ሌላ ፡ ሌላ ፡ ሲል
ሲኮራ ፡ በእንጀራው
እኔ ፡ ግን ፡ ከእጅህ ፡ ነው
ጠግቤ ፡ የምበላው (፪x)
ከእሳት ፡ ይልቅ ፡ የበረታ
ሰልፌ ፡ ኑሮ ፡ ጥዋት ፡ ማታ
ደምህ ፡ ከለላ ፡ ሆኖኝ
እንዳይፈጀኝ ፡ ጠብቆኝ
ተጠነከክልኝና
ባሕሩን ፡ ከፈልከውና
ተሻገርኩኝ ፡ ሄድኩኝ ፡ ማዶ
ነበር ፡ ነገር ፡ ሁሉ ፡ ከብዶ
መች ፡ ቀላል ፡ ሆነና
ያለፍኩት ፡ ጐዳና
ለመኖር ፡ በቃሁኝ
በእጅህ ፡ ተያዝኩና (፪x)
ሳየው ፡ ዞሬ ፡ ወደ ፡ ኋላ
ባይኖረኝ ፡ የአንተ ፡ ከለላ
ተረት ፡ ሆኜ ፡ ቀር ፡ ነበረ
ምሕረትህ ፡ በዛ ፡ ጨመረ
ከፈተና ፡ መውጫ ፡ ብሩ
መኖር ፡ አንተን ፡ እየጠሩ
አታሳፍር ፡ መልስ ፡ አለህ
ለጭንቅ ፡ ቀን ፡ ደራስህ ፡ ነህ
ከጉድጓድ ፡ ከወጡ
ከሞት ፡ ካመለጡ
ከዚህ ፡ በላይ ፡ ደስታ
ምን ፡ አለና ፡ ጌታ (፪x)
ከእናት ፡ በላይ ፡ እናት ፡ ብልህ
ከአባት ፡ በላይ ፡ አባት ፡ ብልህ
አይበቃ ፡ ሥም ፡ ቢሰጥህ
ከዚህ ፡ ሁሉ ፡ የላክ ፡ ነህ
ሳልወድህ ፡ ስለ ፡ ወደድከኝ
ሳልመርጥህ ፡ ስለ ፡ መረጥከኝ
ንጉሥ ፡ ሆይ ፡ እኔም ፡ ምሥጋና ፡ አለኝ
ከነኃጢአቴ ፡ ተቀበልከኝ
ጉድለቴን ፡ የሞላ
አንተን ፡ የለ ፡ ሌላ
ሞገስ ፡ ማዕረጌ ፡ ነህ
ወግ ፡ ያየሁብህ (፪x)
|