ይመጣል (Yemetal) - ካሌብ ፡ ተስፋዬ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ካሌብ ፡ ተስፋዬ
(Caleb Tesfaye)

Caleb Tesfaye 4.jpg


(4)

ተገልብጧል ፡ ታሪክ
(Tegelbetual Tarik)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ ፫ (2000)
ቁጥር (Track):

(5)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የካሌብ ፡ ተስፋዬ ፡ አልበሞች
(Albums by Caleb Tesfaye)

 
አዝ:- ይመጣል ፣ መልስ ፡ ይዞ ፡ ይመጣል
ቀን ፡ ቀጥሯል ፡ ይመጣል ፣ ኑሮን ፡ ያጣፍጣል (፪x)

ሀዘንን ፡ በደስታ ፡ ዋይታንም ፡ በሆታ
ከስቃይ ፡ ገላግሎ ፡ ሊሞላ ፡ በእፎይታ
ታምራቱን ፡ ሊያደርግ ፡ እጅን ፡ በአፍ ፡ ላይ ፡ ሊያስጭን
ሊያስብ ፡ ምስኪኖችን

አዝ:- ይመጣል ፣ መልስ ፡ ይዞ ፡ ይመጣል
ቀን ፡ ቀጥሯል ፡ ይመጣል ፣ ኑሮን ፡ ያጣፍጣል (፪x)

ልጆቹን ፡ ሊያጽናና ፡ ሮሮዋቸውን ፡ ሊያርቅ
ችግርን ፡ ሊመታ ፡ ከጭንቀት ፡ ሊያላቅቅ
ለጠበቁት ፡ ጸንተው ፡ እርሱን ፡ እርሱን ፡ ላሉት
ሲባረኩ ፡ ያያሉ

አዝ:- ይመጣል ፣ መልስ ፡ ይዞ ፡ ይመጣል
ቀን ፡ ቀጥሯል ፡ ይመጣል ፣ ኑሮን ፡ ያጣፍጣል (፪x)

ወጀቡን ፡ ሊገስጽ ፡ አውሎ ፡ ንፋሱንም
ገስግሶ ፡ ሊመጣ ፡ ሳይፈራ ፡ ማንንም
የተናጋን ፡ ኑሮ ፡ ሰላም ፡ ሊዘራበት
አቤት ፡ ሲችልበት

አዝ:- ይመጣል ፣ መልስ ፡ ይዞ ፡ ይመጣል
ቀን ፡ ቀጥሯል ፡ ይመጣል ፣ ኑሮን ፡ ያጣፍጣል (፪x)

መከራም ፡ ነገ ፡ ያልፋል ፡ ችግርም ፡ ይረሳል
የሚያጠግብ ፡ እንጀራ ፡ በአባት ፡ እጁ ፡ ያጐርሳል
በተትረፈረፈ ፣ በሚበቃ ፡ ኑሮ
ያኖራል ፡ አክብሮ

አዝ:- ይመጣል ፣ መልስ ፡ ይዞ ፡ ይመጣል
ቀን ፡ ቀጥሯል ፡ ይመጣል ፣ ኑሮን ፡ ያጣፍጣል (፪x)

እስከመቼ ፡ ድረስ ፡ እናዝናለን ፡ ላሉ
ተዋረድን ፡ አጣን ፡ ተናቅን ፡ ከሰው ፡ ሁሉ
ተስፋ ፡ ለቆረጡ ፡ መልካም ፡ ዜና ፡ አለው
ይላል ፡ ደርሻለሁ

አዝ:- ይመጣል ፣ መልስ ፡ ይዞ ፡ ይመጣል
ቀን ፡ ቀጥሯል ፡ ይመጣል ፣ ኑሮን ፡ ያጣፍጣል (፪x)