ታሪኬ ፡ ተለውጧል (Tarikie Telewetual) - ካሌብ ፡ ተስፋዬ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ካሌብ ፡ ተስፋዬ
(Caleb Tesfaye)

Caleb Tesfaye 4.jpg


(4)

ተገልብጧል ፡ ታሪክ
(Tegelbetual Tarik)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ ፫ (2000)
ቁጥር (Track):

፲ ፩ (11)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የካሌብ ፡ ተስፋዬ ፡ አልበሞች
(Albums by Caleb Tesfaye)

 
አዝ:- ታሪኬ ፡ ተለውጧል ፡ ሌላ ፡ ሰው ፡ ሆኛለሁ
እውነተኛውን ፡ አዳኝ ፡ አግኝቼ ፡ አርፌያለሁ (፪x)

መረጠኝ ፡ ሳልመርጠው ፡ ፈለገኝ ፡ ሳልፈልገው
ከዜምናት ፡ በፊት ፡ ያሰበውን ፡ አደረገው
ማን ፡ ሊከለክለው ፡ ነው ፡ ኧረ ፡ ማን ፡ ሊቃወመው
ኃጢአተኛውን ፡ ወዶት ፡ በደሙ ፡ ከቀደሰው

አዝ:- ታሪኬ ፡ ተለውጧል ፡ ሌላ ፡ ሰው ፡ ሆኛለሁ
እውነተኛውን ፡ አዳኝ ፡ አግኝቼ ፡ አርፌያለሁ (፪x)

የሞት ፡ መውጊያው ፡ ተሰብሮ ፡ ስልጣን ፡ አጣ ፡ በእኔ ፡ ላይ
አልቻለም ፡ ሊያስቀረኝ ፡ ከመንግሥተ ፡ ሰማይ
አልመለስባትም ፡ ወደ ፡ እዚያች ፡ መራራ ፡ ዓለም
ከእንግዲህ ፡ የኢየሱስ ፡ ነኝ ፡ እስከ ፡ ዘለዓለም

አዝ:- ታሪኬ ፡ ተለውጧል ፡ ሌላ ፡ ሰው ፡ ሆኛለሁ
እውነተኛውን ፡ አዳኝ ፡ አግኝቼ ፡ አርፌያለሁ (፪x)

ሳላውቀው ፡ ያሰረኝን ፡ የገዛኝን ፡ ረገጥኩት
ክፉ ፡ ባለጋራዬን ፡ አለሁ ፡ እየተበቀልኩት
ኃይል ፡ አለው ፡ መንፈስ ፡ አለኝ ፡ ባዶዬን ፡ አይደለሁም
ደፍሬው ፡ እዋጋዋለሁኝ ፡ ጠላቴን ፡ አልሸሸውም

አዝ:- ታሪኬ ፡ ተለውጧል ፡ ሌላ ፡ ሰው ፡ ሆኛለሁ
እውነተኛውን ፡ አዳኝ ፡ አግኝቼ ፡ አርፌያለሁ (፪x)

ለክፋት ፡ የፈጠኑት ፡ እግሮቼ ፡ ዛሬ ፡ ሰክነው
ማዳኑን ፡ ለመናገር ፡ ለወንጌል ፡ እየሮጡ ፡ ነው
የታሰሩ ፡ እንዲፈቱ ፡ እንደ ፡ እኔ ፡ እንዲለቀቁ
ከጨለማ ፡ ዓለም ፡ ወጥተው ፡ እንደ ፡ ፀሐይ ፡ እንዲደምቁ

አዝ:- ታሪኬ ፡ ተለውጧል ፡ ሌላ ፡ ሰው ፡ ሆኛለሁ
እውነተኛውን ፡ አዳኝ ፡ አግኝቼ ፡ አርፌያለሁ (፪x)