From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
አዝ:- ሰይጣን ፡ ያሰበው ፡ ያቀደው ፡ ደረሰበት
ስራው ፡ ተበላሸበት ፡ አምላኬ ፡ ደረሰበት
ዲያቢሎስ ፡ ያሰበው ፡ ያቀደው ፡ ደረሰበት
ስራው ፡ ተበላሸበት ፡ ኢየሱስ ፡ ደረሰበት
ሌባው ፡ ሊሰርቅና ፡ ሊያጥፋ ፡ ሲመጣ
ወደ ፡ ሲዖል ፡ ወርውሮ ፡ እኔን ፡ በእሳት ፡ ሊቀጣ
ታዳጊ ፡ አዳኝ ፡ አግኝቼ ፡ ከእጁ ፡ አምልጫለሁ
ከእግሬ ፡ በታች ፡ ወደቀ ፡ እራሱን ፡ ረግጫለሁ
አዝ:- ሰይጣን ፡ ያሰበው ፡ ያቀደው ፡ ደረሰበት
ስራው ፡ ተበላሸበት ፡ አምላኬ ፡ ደረሰበት
ዲያቢሎስ ፡ ያሰበው ፡ ያቀደው ፡ ደረሰበት
ስራው ፡ ተበላሸበት ፡ ኢየሱስ ፡ ደረሰበት
ምኞቱ ፡ አይሞላለትም ፡ ሌት ፡ ተቀር ፡ እሩጫው
ስልት ፡ የሌለው ፡ ወታደር ፡ ተጠፋዉ ፡ ማምለእኛው
እረኛዬ ፡ አይተኛም ፡ ከቶ ፡ አያንቀላፋም
ስራ ፡ ፈቶ ፡ ይልፋ ፡ እንጂ ፡ እኔ ፡ እንደው ፡ አልጠፋም
አዝ:- ሰይጣን ፡ ያሰበው ፡ ያቀደው ፡ ደረሰበት
ስራው ፡ ተበላሸበት ፡ አምላኬ ፡ ደረሰበት
ዲያቢሎስ ፡ ያሰበው ፡ ያቀደው ፡ ደረሰበት
ስራው ፡ ተበላሸበት ፡ ኢየሱስ ፡ ደረሰበት
ኀጢአት ፡ በእኔ ፡ ላይ ፡ ነግሶ ፡ ዐይኔን ፡ አሳውሮት
የኖርኩ ፡ እየመሰለኝ ፡ ሸንጋዩ ፡ እጅ ፡ እግሬን ፡ ይዞት
የጠፉትን ፡ ፈላጊ ፡ ያ ፡ የይሁዳ ፡ አንበሳ
ከመንጋጋው ፡ ነጠቀኝ ፡ ዲያቢሎስ ፡ ድል ፡ ተነሳ
አዝ:- ሰይጣን ፡ ያሰበው ፡ ያቀደው ፡ ደረሰበት
ስራው ፡ ተበላሸበት ፡ አምላኬ ፡ ደረሰበት
ዲያቢሎስ ፡ ያሰበው ፡ ያቀደው ፡ ደረሰበት
ስራው ፡ ተበላሸበት ፡ ኢየሱስ ፡ ደረሰበት
እያባበለ ፡ ወስዶ ፡ ገደል ፡ ሊጨምረኝ
እርሱ ፡ ሊስቅ ፡ ሊደሰት ፡ እኔን ፡ ሊያስለቅሰኝ
መች ፡ እንዳሰበው ፡ ሆነለት ፡ ነገር ፡ ተለወተ
ክፉ ፡ ስራውን ፡ ሊያፈርስ ፡ ኢየሱስ ፡ ተገለጠ
አዝ:- ሰይጣን ፡ ያሰበው ፡ ያቀደው ፡ ደረሰበት
ስራው ፡ ተበላሸበት ፡ አምላኬ ፡ ደረሰበት
ዲያቢሎስ ፡ ያሰበው ፡ ያቀደው ፡ ደረሰበት
ስራው ፡ ተበላሸበት ፡ ኢየሱስ ፡ ደረሰበት (፪x)
|