ሰው ፡ ታደርጋለህ (Sew Tadergaleh) - ካሌብ ፡ ተስፋዬ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ካሌብ ፡ ተስፋዬ
(Caleb Tesfaye)

Caleb Tesfaye 4.jpg


(4)

ተገልብጧል ፡ ታሪክ
(Tegelbetual Tarik)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ ፫ (2000)
ቁጥር (Track):

(2)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የካሌብ ፡ ተስፋዬ ፡ አልበሞች
(Albums by Caleb Tesfaye)

 
አዝ:- ከጢሻ ፡ ከማጥ ፡ ውስጥ ፡ አውጥተህ
በከበረ ፡ ስፍራ ፡ ላይ ፡ ታስቀምጣለህ
ሰው ፡ ታደርጋለህ (ጌታ) ፡ እንዴት ፡ መልካም ፡ ነህ
ሰው ፡ ታደርጋለህ ፡ እንዴት ፡ መልካም ፡ ነህ (ኢየሱስ)
ሰው ፡ ታደርጋለህ ፡ እንዴት ፡ መልካም ፡ ነህ (፪x)

እንደ ፡ እኔ ፡ አይነቱን ፡ ክፉ ፡ ሰው
ከኃጢአተኞች ፡ ሁሉ ፡ የባሰው
እንዴት ፡ አሰብከኝ ፡ መረጥከኝ
ምኔን ፡ አይተህ ፡ ነው ፡ የወደድከኝ
የፍቅርህን ፡ ልክ ፡ ለመግለጽ ፡ ጌታዬ ፡ ቋንቋ ፡ የለኝም
ከስግደት ፡ ከአምልኮ ፡ ሌላ ፡ የምሰጥህ ፡ እኔ ፡ ሌላ ፡ አላገኝም

አዝ:- ከጢሻ ፡ ከማጥ ፡ ውስጥ ፡ አውጥተህ
በከበረ ፡ ስፍራ ፡ ላይ ፡ ታስቀምጣለህ
ሰው ፡ ታደርጋለህ (ጌታ) ፡ እንዴት ፡ መልካም ፡ ነህ
ሰው ፡ ታደርጋለህ ፡ እንዴት ፡ መልካም ፡ ነህ (ኢየሱስ)
ሰው ፡ ታደርጋለህ ፡ እንዴት ፡ መልካም ፡ ነህ (፪x)

እናት ፡ አባት ፡ ሆነኀኛል ፡ እውነተኛ ፡ ወላጅ ፡ ሆንከኝ
እያበላህ ፡ እያጠጣህ ፡ በእቅፍህ ፡ ላይ ፡ አሳደከኝ
ውለታህ ፡ ዝም ፡ አያሰኝም ፡ የደስታ ፡ እምባ ፡ ያመጣል
ያ ፡ ብዙ ፡ ቸርነትህ ፡ ቢወራ ፡ መቼ ፡ ያልቃል

አዝ:- ከጢሻ ፡ ከማጥ ፡ ውስጥ ፡ አውጥተህ
በከበረ ፡ ስፍራ ፡ ላይ ፡ ታስቀምጣለህ
ሰው ፡ ታደርጋለህ (ጌታ) ፡ እንዴት ፡ መልካም ፡ ነህ
ሰው ፡ ታደርጋለህ ፡ እንዴት ፡ መልካም ፡ ነህ (ኢየሱስ)
ሰው ፡ ታደርጋለህ ፡ እንዴት ፡ መልካም ፡ ነህ (፪x)

እኔን ፡ ከድጥ ፡ ላይ ፡ ለማንሳት ፡ ከማንም ፡ ጋር ፡ አልተማከርክ
ልጄ ፡ ነው ፡ ወልጄሃለሁ ፡ ለማለትም ፡ በእኔ ፡ አላፈርክ
በድኔን ፡ አፈር ፡ ልታለብስ ፡ ኑሮዬ ፡ እንዲሆን ፡ ምድር ፡ ሥር
ትንሳኤ ፡ ልትሰጠኝ ፡ እንጂ ፡ አልመጣህ ፡ እኔን ፡ ልትቀብር

አዝ:- ከጢሻ ፡ ከማጥ ፡ ውስጥ ፡ አውጥተህ
በከበረ ፡ ስፍራ ፡ ላይ ፡ ታስቀምጣለህ
ሰው ፡ ታደርጋለህ (ጌታ) ፡ እንዴት ፡ መልካም ፡ ነህ
ሰው ፡ ታደርጋለህ ፡ እንዴት ፡ መልካም ፡ ነህ (ኢየሱስ)
ሰው ፡ ታደርጋለህ ፡ እንዴት ፡ መልካም ፡ ነህ (፪x)

ያለ ፡ መታሰቢያ ፡ እንዳልቀር ፡ ሲኦል ፡ እንዳልወረወር
የሰይጣን ፡ መጫወቻ ፡ እንዳልሆን ፡ እንዳልፈጅብህ ፡ በእቶን
በሕይወት ፡ መዝገብ ፡ ላይ ፡ ስሜን ፡ በከበረው ፡ ደምህ ፡ ጻፍከው
አቤት ፡ የተረሳውን ፡ ሰው ፡ ደግመህ ፡ ወልደህ ፡ ሰው ፡ አደረከው

አዝ:- ከጢሻ ፡ ከማጥ ፡ ውስጥ ፡ አውጥተህ
በከበረ ፡ ስፍራ ፡ ላይ ፡ ታስቀምጣለህ (ጌታ)
ሰው ፡ ታደርጋለህ ፡ እንዴት ፡ መልካም ፡ ነህ
ሰው ፡ ታደርጋለህ ፡ እንዴት ፡ መልካም ፡ ነህ (ኢየሱስ)
ሰው ፡ ታደርጋለህ ፡ እንዴት ፡ መልካም ፡ ነህ (፪x)

ሰው ፡ ታደርጋለህ (ጌታ) ፡ እንዴት ፡ መልካም ፡ ነህ (ኢየሱስ)
ሰው ፡ ታደርጋለህ ፡ እንዴት ፡ መልካም ፡ ነህ (፪x)