From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
"ስለ ፡ ድሆች ፡ መከራ ፡ ስለ ፡ ችግረኞችም ፡ ጩኀት
እግዚአብሔር ፡ አሁን ፡ እነሳለሁ ፡ ይላል
መድሃኒት ፡ አደርጋለሁ ፡ በላይ ፡ በላይ ፡ እገልጣለሁ"
አዝ:- ለችግረኞች ፡ አሁን ፡ እነሳለሁ
ማዳኔን ፡ ይዤ ፡ እገለጣለሁ
የበረታውን ፡ ክንዴን ፡ ያያሉ
በብዙ ፡ ብዙ ፡ ይባረካሉ (፪x)
ተስፋ ፡ የሚያደርጉት ፡ የሚረዳቸው
ከእኔ ፡ በስተቀር ፡ ማንም ፡ የላቸው
. (1) . ፡ ተሞልተው ፡ ጠርተዉኛል
ቶሎ ፡ ድረስልን ፡ ብለውኛል
ያለቀሱትን ፡ ለቅሶ ፡ አይቻለሁ
ጸሎታቸውን ፡ ሰምቼዋለሁ
ከእንግዲህ ፡ ላይራቡ ፡ ልጆቼ
ጥላ ፡ ባመጡላቸው ፡ እጆቼ
አዝ:- ለችግረኞች ፡ አሁን ፡ እነሳለሁ
ማዳኔን ፡ ይዤ ፡ እገለጣለሁ
የበረታውን ፡ ክንዴን ፡ ያያሉ
በብዙ ፡ ብዙ ፡ ይባረካሉ (፪x)
መከራው ፡ በዝቶ ፡ ብዙ ፡ ተማረው
ያለ ፡ ልክ ፡ አጥተው ፡ ተቸግረው
ሞትን ፡ ሲመርጡ ፡ ከመኖር ፡ ይልቅ
ያላቸው ፡ ሁሉ ፡ ተሟጦ ፡ ሲያልቅ
በከንቱ ፡ ሲጨነቁ ፡ አየኋቸው
እኔን ፡ የሚያክል ፡ ጌታ ፡ እያላቸው
ስቃያቸውን ፡ አንጀቴ ፡ አልቻለም
በቃ ፡ ብያለሁ ፡ ከእንግዲህ ፡ ሃዘን ፡ የለም
አዝ:- ለችግረኞች ፡ አሁን ፡ እነሳለሁ
ማዳኔን ፡ ይዤ ፡ እገለጣለሁ
የበረታውን ፡ ክንዴን ፡ ያያሉ
በብዙ ፡ ብዙ ፡ ይባረካሉ (፪x)
ሁሉ ፡ እቋቸው ፡ ብቸኛ ፡ ሆነው
የሚደርስልን ፡ ኧረ ፡ ማነው
ወዳች ፡ ዘመዶቻቸው ፡ ሸሿቸው
አናውቃችሁም ፡ ብለው ፡ ካዷቸው
ያጥላሏቸውን ፡ አሳፍራለው
እንደተናቁ ፡ መች ፡ አስቀራለው
ወዮ ፡ ባሉበት ፡ አንደበታቸው
ሰው ፡ ሁሉ ፡ ያያል ፡ ሳዘምራቸው
አዝ:- ለችግረኞች ፡ አሁን ፡ እነሳለሁ
ማዳኔን ፡ ይዤ ፡ እገለጣለሁ
የበረታውን ፡ ክንዴን ፡ ያያሉ
በብዙ ፡ ብዙ ፡ ይባረካሉ (፪x)
እንጀራ ፡ ለአጡ ፡ መጋቢያቸው ፡ ነኝ
ለተጠሙ ፡ ሁሉ ፡ የሚጠታ ፡ አለኝ
ወዴኔ ፡ መጥተው ፡ ከቶ ፡ አያፍሩም
የለመኑኝን ፡ አንዳች ፡ አያጡም
ለጠሩኝ ፡ ሁሉ ፡ ባለጠጋ ፡ ነኝ
የምስኪኖችን ፡ እምባ ፡ አባሽ ፡ ነኝ
ሁሉን ፡ ሸለቆን ፡ መሙላት ፡ አውቃለሁ
ችግረኞችን ፡ እባርካለው
አዝ:- ለችግረኞች ፡ አሁን ፡ እነሳለሁ
ማዳኔን ፡ ይዤ ፡ እገለጣለሁ
የበረታውን ፡ ክንዴን ፡ ያያሉ
በብዙ ፡ ብዙ ፡ ይባረካሉ (፪x)
|