From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
አዝ:- ልብ ፡ ለልብ ፡ ተከባብደን ፡ እንዴት ፡ ይኖራል
ያለ ፡ ፍቅር ፡ ክርስትና ፡ ምን ፡ ይረባናል
እወድሃለሁ/እወድሻለሁ ፡ እያሉ ፡ መሸነጋገል
ከንቱ ፡ ነው ፡ ሰው ፡ እየጠሉ ፡ ጌታን ፡ ማገልገል (፪x)
በአንድ ፡ ልብ ፡ አብሮ ፡ መኖርን ፡ እንለማመድ
መከፋፈሉ ፡ ይበቃናል ፡ ተዉ ፡ እንዋደድ
መራራቁም ፡ እየሰፋ ፡ እንዳንለያይ
እንሰባሰብ ፡ እናምልክ ፡ ጌታን ፡ በአንድ ፡ ላይ
አዝ:- ልብ ፡ ለልብ ፡ ተከባብደን ፡ እንዴት ፡ ይኖራል
ያለ ፡ ፍቅር ፡ ክርስትና ፡ ምን ፡ ይረባናል
እወድሃለሁ/እወድሻለሁ ፡ እያሉ ፡ መሸነጋገል
ከንቱ ፡ ነው ፡ ሰው ፡ እየጠሉ ፡ ጌታን ፡ ማገልገል (፪x)
በቤት ፡ ሌላ ፡ ውጪ ፡ ሌላ ፡ ሁለት ፡ ዐይነት ፡ ሰው
ችላ ፡ እያልን ፡ ትዕዛዛቱን ፡ እየረሳነው
ሁሌ ፡ ወተት ፡ እየተጋትን ፡ እየጫጨን ፡ ነው
ዛሬ ፡ እንወስን ፡ እንለወጥ ፡ ለእርሱ ፡ እንመቸው
አዝ:- ልብ ፡ ለልብ ፡ ተከባብደን ፡ እንዴት ፡ ይኖራል
ያለ ፡ ፍቅር ፡ ክርስትና ፡ ምን ፡ ይረባናል
እወድሃለሁ/እወድሻለሁ ፡ እያሉ ፡ መሸነጋገል
ከንቱ ፡ ነው ፡ ሰው ፡ እየጠሉ ፡ ጌታን ፡ ማገልገል (፪x)
ሲቀርቡ ፡ ሳቅ ፡ ሲርቁ ፡ ሃሜት ፡ ልማድ ፡ አድርገነው
ጌታ ፡ እንዳያልፍ ፡ እንዳይሰራ ፡ እጁን ፡ ይዘነው
ከአንገት ፡ በላይ ፡ ወድሃለሁ ፡ ይህም ፡ አለማድላት
እውነተኛይቱን ፡ ፍቅር ፡ ወዴት ፡ አደረግናት
አዝ:- ልብ ፡ ለልብ ፡ ተከባብደን ፡ እንዴት ፡ ይኖራል
ያለ ፡ ፍቅር ፡ ክርስትና ፡ ምን ፡ ይረባናል
እወድሃለሁ/እወድሻለሁ ፡ እያሉ ፡ መሸነጋገል
ከንቱ ፡ ነው ፡ ሰው ፡ እየጠሉ ፡ ጌታን ፡ ማገልገል (፪x)
በቃል ፡ ብቻ ፡ አኗደድ ፡ ተግባር ፡ ይጨመር
ፍቅራችንን ፡ ሁሉ ፡ እንዲያውቀው ፡ እያደር ፡ ይመር
እጅ ፡ ለእጅ ፡ እንያያዝ ፡ ስራም ፡ እንስራ
ጠላት ፡ መግቢያ ፡ ቀዳዳ ፡ አያግኝ ፡ እኛን ፡ ሲያይ ፡ ይፍራ
አዝ:- ልብ ፡ ለልብ ፡ ተከባብደን ፡ እንዴት ፡ ይኖራል
ያለ ፡ ፍቅር ፡ ክርስትና ፡ ምን ፡ ይረባናል
እወድሃለሁ/እወድሻለሁ ፡ እያሉ ፡ መሸነጋገል
ከንቱ ፡ ነው ፡ ሰው ፡ እየጠሉ ፡ ጌታን ፡ ማገልገል (፪x)
|