ከአንተ ፡ በላይ (Kante Belay) - ካሌብ ፡ ተስፋዬ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ካሌብ ፡ ተስፋዬ
(Caleb Tesfaye)

Caleb Tesfaye 4.jpg


(4)

ተገልብጧል ፡ ታሪክ
(Tegelbetual Tarik)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ ፫ (2000)
ቁጥር (Track):

(8)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የካሌብ ፡ ተስፋዬ ፡ አልበሞች
(Albums by Caleb Tesfaye)

 
ሰማይ ፡ ሆነ ፡ ምድር ፡ ጌታ ፡ ሆኖ ፡ የሚመለከው
ስግደት ፡ የተገባው ፡ . (1) . ፡ ያለኸው
ዓይናችን ፡ በራልን ፡ ማን ፡ አዳኝ ፡ እንደሆነ ፡ አየን
ስምህ ፡ ክብራችን ፡ ነው ፡ የአንተ ፡ ነን ፡ አንኮራለን
እውነተኛው ፡ አምላክ ፡ ለህዝቦችህ ፡ ያለህ

አዝ:- ከአንተ ፡ በላይ ፡ አምላክ ፡ የለም ፡ ከአንተ ፡ በላይ (፰x)

ስንቱን ፡ ደፋርና ፡ ትዕቢተኛን ፡ ጥለሃል
በውጊያ ፡ ሜዳ ፡ ላይ ፡ ቁጣህም ፡ ታይቶልሃል
ሞኛሞኞች ፡ ሆነው ፡ ሊጣሉህ ፡ መጡ ፡ ታጥቀው
የውርደት ፡ አቧራ ፡ ከደናቸው ፡ . (2) .
ጀግና ፡ ነው ፡ አርሱ ፡ አሉ ፡ . (3) . ፡ ጌታቸው

አዝ:- ከአንተ ፡ በላይ ፡ ጀግና ፡ የለም ፡ ከአንተ ፡ በላይ (፰x)

ወልደህ ፡ እንደሰው ፡ ምድረ ፡ በዳ ፡ ላይ ፡ አትጥልም
እንጀራም ፡ እያለ ፡ ድንጋይ ፡ ብላ ፡ አትልም
የወላጅ ፡ አንጀትህ ፡ ይንሰፈሰፍልናል
ብሩካን ፡ እጆችህ ፡ ቆርሰው ፡ ይመግቡናል
እንደአንተ ፡ ያለ ፡ አባት ፡ የትስ ፡ ይገኝልናል

አዝ:- ከአንተ ፡ በላይ ፡ አባት ፡ የለም ፡ ከአንተ ፡ በላይ (፰x)

ለበሽታ ፡ ሁሉ ፡ ፍቱን ፡ መድሃኒት ፡ አለህ
ሞት ፡ አፋፍ ፡ ላይ ፡ ላሉ ፡ ብቸኛ ፡ መልስ ፡ አንተ ፡ ነህ
በእጆችህ ፡ ተዳሰው ፡ አፎይ ፡ ያሉ ፡ ብዙ ፡ አሉ
ሌት ፡ ተቀን ፡ ከማልቀስ ፡ ክእንባ ፡ የተገላገሉ
ይኸው ፡ ተፈውሰው ፡ ለክብርህ ፡ ይዘምራሉ

አዝ:- ከአንተ ፡ በላይ ፡ ፈዋሽ ፡ የለም ፡ ከአንተ ፡ በላይ (፰x)

"ሃሌሉያ ፡ በሰማይ ፡ በምድር ፡ ቢሆን
እንደ ፡ አንተ ፡ ያለ ፡ ማንም ፡ የለም ፡ ጌታ ፡ ሆይ
ከምድር ፡ ጫፍ ፡ እስከምድር ፡ ጫፍ
ታላቁ ፡ ሥምህ ፡ የተባረከ ፡ ይሁን"

ሃሌሉያ(፲፮x)